La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 13:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ካህ​ኑም በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ቈረ​ቈ​ሩን ያያል፤ እነ​ሆም፥ ከተ​ላጨ በኋላ ቈረ​ቈሩ በቆ​ዳው ላይ ባይ​ሰፋ፥ መል​ኩም ወደ ቆዳው ባይ​ጠ​ልቅ፥ ካህኑ፦ ‘ንጹሕ ነው’ ይለ​ዋል፤ ልብ​ሱን አጥቦ ንጹሕ ይሆ​ናል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ካህኑ በሰባተኛው ቀን የሚያሳክከውን የሰውየውን ቍስል ይመርምር፤ በቈዳው ላይ ካልሰፋና ከቈዳው በታች ዘልቆ ካልገባ ካህኑ ያ ሰው ንጹሕ መሆኑን ያስታውቅ፤ ልብሱን ዐጥቦ ንጹሕ ይሁን።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ካህኑም በሰባተኛው ቀን ቈረቈሩን ያያል፤ እነሆም፥ ቈረቈሩ በቆዳው ላይ ባይሰፋ፥ ከቆዳውም በታች ዘልቆ ባይታይ፥ ካህኑ፦ ንጹሕ ነው ይለዋል፤ ልብሱንም ያጥብና ንጹሕ ይሆናል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በሰባተኛውም ቀን እንደገና ካህኑ ቊስሉን ይመርምር፤ ቊስሉ በመስፋፋት ላይ ካልተገኘና በዙሪያውም ካለው የሰውነቱ ቆዳ ይልቅ የጐደጐደ ካልሆነ ያ ሰው የነጻ መሆኑን ያስታውቅለት፤ ሰውየው ልብሱን ይጠብ፤ ንጹሕም ይሆናል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ካህኑም በሰባተኛው ቀን ቈረቈሩን ያያል፤ እነሆም፥ ቈረቈሩ በቁርበቱ ላይ ባይሰፋ፥ መልኩም ወደ ቁርበቱ ባይጠልቅ፥ ካህኑ፦ ንጹሕ ነው ይለዋል፤ ልብሱን አጥቦ ንጹሕ ይሆናል።

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 13:34
6 Referencias Cruzadas  

እነ​ሆም፥ ወደ ቆዳው ቢጠ​ልቅ፥ በው​ስ​ጡም ቀጭን ብጫ ጠጕር ቢኖ​ር​በት፥ ካህኑ፦ ‘ርኩስ ነው’ ይለ​ዋል፤ ቈረ​ቈር ነው፤ የራስ ወይም የአ​ገጭ ለምጽ ነው።


ቈረ​ቈሩ ግን አይ​ላ​ጭም፤ ካህ​ኑም ቈር​ቈር ያለ​በ​ትን ሰው ሰባት ቀን ደግሞ ይለ​የ​ዋል።


ከነጻ በኋላ ግን ቈረ​ቈሩ በቆ​ዳው ላይ ቢሰፋ፥ ካህኑ ያየ​ዋል፤


ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።


አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፤ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ፤


“ሥራህንና ድካምህን ትዕግሥትህንም አውቃለሁ፤ ክፉዎችንም ልትታገሥ እንዳትችል፥ እንዲሁም ሳይሆኑ ‘ሐዋርያት ነን’ የሚሉቱን መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸው አውቃለሁ፤