ይሁዳም አይቶ “ከእኔ ይልቅ ትዕማር እውነተኛ ሆነች፤ ልጄን ሴሎምን አልሰጠኋትምና” አለ። ትገደል ማለትንም ተወ፤ ደግሞም አላወቃትም።
ዘሌዋውያን 13:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያች ደዌ ግን በስፍራዋ ብትቆም፥ ባትሰፋም፥ የቍስል እትራት ናት፤ ካህኑም፦ ‘ንጹሕ ነው’ ይለዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቋቍቻው ግን ባለበት ከቈየና ወደ ሌላ ስፍራ ካልተስፋፋ፣ የዕባጩ ጠባሳ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ካህኑም ንጹሕ መሆኑን ያስታውቅ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቋቁቻው ግን በስፍራው ቢቆም ባይሰፋም፥ የብጉንጅ ቁስል ጠባሳ ነው፤ ካህኑም፦ ንጹሕ ነው ይለዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ቋቁቻው ምንም ለውጥ ሳያደርግና ሳይስፋፋ ቢገኝ የእባጭ ጠባሳ መሆኑ ታውቆ መንጻቱን ካህኑ ያስታውቅለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቍቁቻው ግን በስፍራው ቢቆም ባይሰፋም፥ የቍስል ጠባሳ ነው፤ ካህኑም፦ ንጹሕ ነው ይለዋል። |
ይሁዳም አይቶ “ከእኔ ይልቅ ትዕማር እውነተኛ ሆነች፤ ልጄን ሴሎምን አልሰጠኋትምና” አለ። ትገደል ማለትንም ተወ፤ ደግሞም አላወቃትም።
ዳዊትም ናታንን፥ “እግዚአብሔርን በድያለሁ” አለው። ናታንም ዳዊትን አለው፥ “እግዚአብሔር ደግሞ ኀጢአትህን አርቆልሃል፤ አትሞትምም።
ካህኑም ቢያየው፥ በቋቍቻውም ነጭ ጠጕር ባይኖር፥ ወደ ቆዳውም ባይጠልቅ፥ ነገር ግን ቢከስም፥ ካህኑ ሰባት ቀን ይለየዋል።
ወንድሞቻችን ሆይ፥ ከእናንተ ወገን የተሳሳተ ሰው ቢኖር በመንፈስ ቅዱስ የጸናችሁ እናንት እንዳትሳሳቱ ለራሳችሁ እየተጠበቃችሁ፥ እንደዚህ ያለውን ሰው ቅንነት ባለው ልቡና አጽኑት።