“ሰው በሥጋው ቆዳ ላይ እባጭ ብትወጣበት፥ ብትነጣም፥ በሥጋውም ቆዳ እንደ ለምጽ ደዌ ብትመስል፥ ወደ ካህኑ ወደ አሮን ወይም ከካህናቱ ልጆች ወደ አንዱ ያምጡት።
ዘሌዋውያን 13:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቆዳውም ላይ ቢሰፋ፥ ካህኑ፦ ‘ርኩስ ነው’ ይለዋል፤ የለምጽ ደዌ ነው፤ በእትራቱ ላይ ወጥቶአልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቈዳው ላይ ተስፋፍቶ ካገኘውም፣ ርኩስ መሆኑን ካህኑ ያስታውቅ፤ የሚተላለፍ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቆዳውም ላይ ቢስፋፋ፥ ካህኑ፦ ርኩስ ነው ይለዋል፤ ደዌ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቊስሉ ያለበትም ቦታ እየሰፋ መሄዱ ከታወቀ፥ ያ የሥጋ ደዌ ስለ ሆነ ርኩስ መሆኑን ያስታውቅ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቁርበቱም ላይ ቢሰፋ፥ ካህኑ፦ ርኩስ ነው ይለዋል፤ ደዌ ነው። |
“ሰው በሥጋው ቆዳ ላይ እባጭ ብትወጣበት፥ ብትነጣም፥ በሥጋውም ቆዳ እንደ ለምጽ ደዌ ብትመስል፥ ወደ ካህኑ ወደ አሮን ወይም ከካህናቱ ልጆች ወደ አንዱ ያምጡት።