Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘሌዋውያን 13:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ያች ደዌ ግን በስ​ፍ​ራዋ ብት​ቆም፥ ባት​ሰ​ፋም፥ የቍ​ስል እት​ራት ናት፤ ካህ​ኑም፦ ‘ንጹሕ ነው’ ይለ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ቋቍቻው ግን ባለበት ከቈየና ወደ ሌላ ስፍራ ካልተስፋፋ፣ የዕባጩ ጠባሳ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ካህኑም ንጹሕ መሆኑን ያስታውቅ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ቋቁቻው ግን በስፍራው ቢቆም ባይሰፋም፥ የብጉንጅ ቁስል ጠባሳ ነው፤ ካህኑም፦ ንጹሕ ነው ይለዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ነገር ግን ቋቁቻው ምንም ለውጥ ሳያደርግና ሳይስፋፋ ቢገኝ የእባጭ ጠባሳ መሆኑ ታውቆ መንጻቱን ካህኑ ያስታውቅለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ቍቁቻው ግን በስፍራው ቢቆም ባይሰፋም፥ የቍስል ጠባሳ ነው፤ ካህኑም፦ ንጹሕ ነው ይለዋል።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 13:23
13 Referencias Cruzadas  

ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ከእ​ና​ንተ ወገን የተ​ሳ​ሳተ ሰው ቢኖር በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የጸ​ና​ችሁ እና​ንት እን​ዳ​ት​ሳ​ሳቱ ለራ​ሳ​ችሁ እየ​ተ​ጠ​በ​ቃ​ችሁ፥ እን​ደ​ዚህ ያለ​ውን ሰው ቅን​ነት ባለው ልቡና አጽ​ኑት።


ደግ​ሞም እን​ዲህ ያለው ሰው ከኀ​ዘን ብዛት የተ​ነሣ እን​ዳ​ይ​ዋጥ ይቅር ልት​ሉ​ትና ልታ​ጽ​ና​ኑት ይገ​ባል።


ጴጥሮስም “ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ፤” ያለው የኢየሱስ ቃል ትዝ አለው፤ ወደ ውጭም ወጥቶ መራራ ልቅሶ አለቀሰ።


ዳዊ​ትም ናታ​ንን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በድ​ያ​ለሁ” አለው። ናታ​ንም ዳዊ​ትን አለው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደግሞ ኀጢ​አ​ት​ህን አር​ቆ​ል​ሃል፤ አት​ሞ​ት​ምም።


ይሁ​ዳም አይቶ “ከእኔ ይልቅ ትዕ​ማር እው​ነ​ተኛ ሆነች፤ ልጄን ሴሎ​ምን አል​ሰ​ጠ​ኋ​ት​ምና” አለ። ትገ​ደል ማለ​ት​ንም ተወ፤ ደግ​ሞም አላ​ወ​ቃ​ትም።


በቆ​ዳ​ውም ላይ ቢሰፋ፥ ካህኑ፦ ‘ርኩስ ነው’ ይለ​ዋል፤ የለ​ምጽ ደዌ ነው፤ በእ​ት​ራቱ ላይ ወጥ​ቶ​አ​ልና።


“በሥ​ጋ​ውም ቆዳ የእ​ሳት ትኩ​ሳት ቢኖ​ር​በት፥ በተ​ቃ​ጠ​ለ​ውም ስፍራ ነጭ፥ ወይም ቀላ ያለ ቋቍቻ ቢታይ፥


ካህ​ኑም ቢያ​የው፥ በቋ​ቍ​ቻ​ውም ነጭ ጠጕር ባይ​ኖር፥ ወደ ቆዳ​ውም ባይ​ጠ​ልቅ፥ ነገር ግን ቢከ​ስም፥ ካህኑ ሰባት ቀን ይለ​የ​ዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios