ዘሌዋውያን 13:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቍስሉም ስፍራ ነጭ እባጭ ወይም ቀላ ያለ ቋቍቻ ቢወጣ፥ በካህኑ ዘንድ ይታያል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕባጩ በነበረበት ቦታ ላይም ነጭ ዕብጠት ወይም ነጣ ያለ ቀይ ቋቍቻ ቢታይ፣ ካህኑ ዘንድ ይቅረብ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በብጉንጁም የቁስል ስፍራ ላይ ነጭ እባጭ ወይም ነጣ ብሎ ቀላ ያለ ቋቁቻ ቢወጣ፥ በካህኑ ዘንድ ይታያል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዘግየት ብሎም ቊስሉ ባለበት ቦታ ነጭ እባጭ ወይም ቀላ ያለ ቋቁቻ ዐይነት ቊስል ቢወጣበት ወደ ካህኑ ይሂድ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቍስሉም ስፍራ ነጭ እባጭ ወይም ቀላ ያለ ቍቁቻ ቢወጣ፥ በካህኑ ዘንድ ይታያል። |
ካህኑም ያያል፤ እነሆም፥ ወደ ቆዳው ውስጥ ጠልቆ ቢታይ፥ ጠጕሩም ተለውጦ ቢነጣ፥ ካህኑ፦ ‘ርኩስ ነው’ ይለዋል፤ የለምጽ ደዌ ነው፤ ከቍስሉ ውስጥ ወጥቶአል።
ካህኑም ያየዋል፤ እነሆም፥ የደዌው እብጠት በሥጋው ቆዳ ላይ የሆነ ለምጽ መስሎ፥ በቡሀነቱ ወይም በራሰ በራነቱ ነጭ ወይም ቀላ ያለ ቢሆን፥
የለምጹንም ምልክት ያያል፤ እነሆም፥ የለምጹ ምልክት በግንቡ ላይ በአረንጓዴና በቀይ ቢዥጐረጐር፥ መልኩም ወደ ግንቡ ውስጥ ቢጠልቅ፥