ዘሌዋውያን 12:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከደምዋም እስክትነጻ ሠላሳ ሦስት ቀን ትቈይ፤ የመንጻቷ ቀንም እስኪፈጸም ድረስ የተቀደሰን ነገር አትንካ፤ ወደ መቅደስም አትግባ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴትዮዋም ከደሟ እስክትነጻ ድረስ ሠላሳ ሦስት ቀን ትቈይ፤ የመንጻቷም ወራት እስኪፈጸም ድረስ ማንኛውንም የተቀደሰ ነገር አትንካ፤ ወደ ቤተ መቅደስም አትግባ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከደምዋም እስክትነጻ ሠላሳ ሦስት ቀን ትቀመጥ፤የመንጻትዋ ቀንም እስኪፈጸም ድረስ የተቀደሰን ነገር ሁሉ አትንካ፥ ወደ መቅደስም አትግባ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ በተጨማሪ ደምዋ እስከሚጠራ እስከ ሠላሳ ሦስት ቀን ድረስ የተቀደሰውን ማናቸውንም ነገር መንካት የለባትም፤ ይህ የመንጻትዋም ጊዜ እስከሚፈጸም ድረስ ወደ ተቀደሰው ድንኳን አትግባ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከደምዋም እስክትነጻ ሠላሳ ሦስት ቀን ትቀመጥ፤ የመንጻትዋ ቀንም እስኪፈጸም ድረስ የተቀደሰን ነገር አትንካ፥ ወደ መቅደስም አትግባ። |
ሴት ልጅም ብትወልድ እንደ ግዳጅዋ ወራት ሁለት ሳምንት ያህል የረከሰች ናት፤ ከደምዋም እስክትነጻ ድረስ ስድሳ ስድስት ቀን ትቈይ።