እግዚአብሔርም አለ፥ “ውኃ የሕይወት እስትንፋስ ያላቸውን ተንቀሳቃሾችና በምድር ላይ ከሰማይ በታች የሚበርሩ አዕዋፍን ታስገኝ፥” እንዲሁም ሆነ።
ዘሌዋውያን 11:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በምድርም ላይ የሚንቀሳቀስ ተንቀሳቃሽ አውሬ ሁሉ ለእናንተ ርኩስ ነው፤ አትብሉትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ምድር ለምድር የሚንቀሳቀስ ማንኛውም ፍጡር ጸያፍ ነው፤ አይበላም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በምድርም ላይ የሚርመሰመስ ተንቀሳቃሽ ሁሉ ጸያፍ ነው፥ አይበላም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በምድር ላይ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ትናንሽ ነፍሳት ሁሉ የማይበሉና በእናንተ ዘንድ የተጠሉ ይሁኑ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድርም ላይ የሚንቀሳቀስ ተንቀሳቃሽ ሁሉ የተጸየፈ ነው፥ አትብሉትም። |
እግዚአብሔርም አለ፥ “ውኃ የሕይወት እስትንፋስ ያላቸውን ተንቀሳቃሾችና በምድር ላይ ከሰማይ በታች የሚበርሩ አዕዋፍን ታስገኝ፥” እንዲሁም ሆነ።
በምድር ላይ ሥጋ ያለው የሚንቀሳቀሰው ሁሉ ወፉም፥ እንስሳውም፥ አራዊቱም፥ በምድር ላይ የሚርመሰመሰው ተንቀሳቃሹምሁሉ፥ ሰውም ሁሉ ጠፋ።
“በምድር ላይም ከሚንቀሳቀስ ተንቀሳቃሽ እነዚህ ለእናንተ ርኩሳን ናቸው፤ ሙጭልጭላ፥ አይጥ፥ እንሽላሊት በየወገኑ፥
በሆዱ የሚሳብ፥ በአራትም እግሮች የሚሳብ፥ ብዙ እግሮችም ያሉት፥ በምድርም ላይ የሚንቀሳቀሱ ተንቀሳቃሾች ሁሉ ርኩሳን ናቸውና አትብሉአቸው።