ከእነዚህም በድን የሚወድቅበት ሁሉ ርኩስ ነው፤ እቶን ወይም ምድጃ ቢሆን ይሰባበራል፤ ርኩሳን ናቸውና፤ ለእናንተ ርኩሳን ይሆናሉ።
ዘሌዋውያን 11:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ምንጩ፥ ጉድጓዱም፥ የውኃውም ኵሬ ንጹሓን ናቸው፤ በድናቸውን ግን የሚነካ ርኩስ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ምንጭ ወይም የውሃ ማጠራቀሚያ ጕድጓድ ንጹሕ እንደ ሆነ ይቈያል፤ ሆኖም በድኑን የነካ ይረክሳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ምንጭና የውኃ ማጠራቀምያ ጉድጓድ ንጹሕ ይሆናሉ፤ በድናቸውን ግን የሚነካ ርኩስ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌላው ነገር ሁሉ የእነዚህ እንስሶች በድን ሲነካው የሚረክስ ቢሆንም ምንጭ ወይም የውሃ ጒድጓድ አይረክስም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ምንጩ፥ ጕድጓዱም፥ የውኃውም ኩሬ ንጹሐን ናቸው፤ በድናቸውን ግን የሚነካ ርኩስ ነው። |
ከእነዚህም በድን የሚወድቅበት ሁሉ ርኩስ ነው፤ እቶን ወይም ምድጃ ቢሆን ይሰባበራል፤ ርኩሳን ናቸውና፤ ለእናንተ ርኩሳን ይሆናሉ።
እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ግን ለዘለዓለም አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውኃ በውስጡ ለዘለዓለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆንለታል እንጂ።”