ዘሌዋውያን 11:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚበርር፥ አራትም እግሮች ያሉት ተንቀሳቃሽ ሁሉ ለእናንተ ርኩስ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ክንፍ ኖሯቸው በአራት እግር የሚንቀሳቀሱትን ፍጥረታት ተጸየፏቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ሌሎች አራት እግሮች ያሉአቸው ጥቃቅን በራሪ ነፍሳት ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፉ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ሌሎች ክንፎችና አራት እግሮች ያሉአቸው ፍጥረቶች እንደ ርኩስ ይቈጠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን የሚበርር፥ አራትም እግሮች ያሉት ተንቀሳቃሽ ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፈ ነው። |
ከእነርሱም እነዚህን አትበሉም፤ ኩብኩባ የሚመስለውም፥ ፌንጣ የሚመስለውም፥ አሸን የሚመስለውም፥ አንበጣ የሚመስለውም።
በአራት እግሮቹ ከሚሄድ እንስሳ ሁሉ በመዳፎቹ ላይ የሚሄድ ለእናንተ ርኩስ ነው፤ የእርሱን በድን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።