ሁለት ወይፈኖች ይሰጡን፤ እነርሱም አንድ ወይፈን ይምረጡ፤ እየብልቱም ይቍረጡት፤ በእንጨትም ላይ ያኑሩት፤ በበታቹም እሳት አይጨምሩ፤ እኔም ሁለተኛውን ወይፈን አዘጋጃለሁ፤ በእንጨቱም ላይ አኖረዋለሁ፤ በበታቹም እሳት አልጨምርም።
ዘሌዋውያን 1:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአሮንም ልጆች ካህናቱ የተቈረጡትን ብልቶች፥ ራሱንም፥ ስቡንም በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በዕንጨቱ ላይ ይረበርቡታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህናቱ የአሮን ልጆች ጭንቅላቱንና ሥቡን ጨምረው ብልቶቹን በመሠዊያው ላይ በሚነድደው ዕንጨት ላይ ይደርድሩት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአሮንም ልጆች ካህናቱ ብልቶቹንና ራሱን ስቡንም በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በእንጨቱ ላይ ይረበርቡታል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእንስሳውንም ሥጋ ብልቶች በየዐይነታቸው ለያይተው ራሱንና ስቡንም ጭምር በመሠዊያው ላይ በተረበረበው እንጨት ላይ ያኑሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአሮንም ልጆች ካህናቱ የተቈረጡትን ብልቶች ራሱንም ስቡንም በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በእንጨቱ ላይ ይረበርቡታል፤ |
ሁለት ወይፈኖች ይሰጡን፤ እነርሱም አንድ ወይፈን ይምረጡ፤ እየብልቱም ይቍረጡት፤ በእንጨትም ላይ ያኑሩት፤ በበታቹም እሳት አይጨምሩ፤ እኔም ሁለተኛውን ወይፈን አዘጋጃለሁ፤ በእንጨቱም ላይ አኖረዋለሁ፤ በበታቹም እሳት አልጨምርም።
በዙሪያውም በስተውስጥ የነበረው የለዘበ ከንፈራቸው አንድ ጋት ነበረ፤ በገበታውም ላይ መክደኛ ነበረ፤ ከፀሐይና ከዝናምም የተሰወረ ነበረ።
በየብልቱም ራሱን፥ ስቡንም ይቈርጡታል፤ ካህናቱም በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በዕንጨቱ ላይ ይረበርቡታል፤
ከደኅንነቱም መሥዋዕት ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን አድርገው ያቀርባሉ፤ የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ፥ በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥
ሁለቱንም ኵላሊቶች፥ በእነርሱም ላይና በጎድኑ አጠገብ ያለውን ስብ፥ በጉበቱም ላይ ያለውን መረብ ከኵላሊቶቹ ጋር ያመጣሉ።