እግዚአብሔር ወዳለውም ወደዚያ ቦታ ደረሱ፤ አብርሃምም በዚያ መሠዊያዉን ሠራ፤ ዕንጨትንም ረበረበ፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ በመሠዊያዉ በዕንጨቱ ላይ በልቡ አስተኛው።
ዘሌዋውያን 1:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የካህኑም የአሮን ልጆች በመሠዊያው ላይ እሳት ያነድዳሉ፤ በእሳቱም ላይ ዕንጨት ይረበርባሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የካህኑ የአሮን ልጆች በመሠዊያው ላይ ዕንጨት ረብርበው እሳት ያንድዱበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የካህኑም የአሮን ልጆች በመሠዊያው ላይ እሳት ያነድዳሉ፥ በእሳቱም ላይ እንጨት ይደረድራሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የካህኑ የአሮን ዘሮች የሆኑትም ካህናት በመሠዊያው ላይ እንጨት ረብርበው እሳት ያቀጣጥሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የካህኑም የአሮን ልጆች በመሠዊያው ላይ እሳት ያነድዳሉ፥ በእሳቱም ላይ እንጨት ይደረድራሉ፤ |
እግዚአብሔር ወዳለውም ወደዚያ ቦታ ደረሱ፤ አብርሃምም በዚያ መሠዊያዉን ሠራ፤ ዕንጨትንም ረበረበ፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ በመሠዊያዉ በዕንጨቱ ላይ በልቡ አስተኛው።
ዳዊትም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱንም መሥዋዕት አቀረበ፤ እግዚአብሔርንም ጠራ፤ ከሰማይም ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ በእሳት መለሰለት፤ እሳቱም የሚቃጠለውን መሥዋዕት በላ።
ሰሎሞንም ይህን ጸሎት በፈጸመ ጊዜ እሳት ከሰማይ ወርዶ የሚቃጠለውን ቍርባንና መሥዋዕቱን ሁሉ በላ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ቤቱን ሞላ።
በየጊዜውም ዕንጨት ለሚሸከሙ ሰዎች ቍርባን፥ ለበኵራቱም ሥርዐት አደረግሁ። “አምላካችን ሆይ፥ በመልካም አስበኝ።”
እሳትም ከእግዚአብሔር ዘንድ ወጣ፤ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ ስቡንም በላ፤ ሕዝቡም ሁሉ አይተው ተደነቁ፤ በግምባራቸውም ወደቁ።
በመሠዊያዬ ላይ እሳትን በከንቱ እንዳታቃጥሉ ከእናንተ ዘንድ ደጅ የሚዘጋ ሰው ምነው በተገኘ! በእናንተ ደስ አይለኝም፥ ቍርባንንም ከእጃችሁ አልቀበልም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።