በጠራሁና በጮኽሁ ጊዜ ጸሎቴ ተከለከለ።
ርዳታ ፈልጌ ብጣራና ብጮኽ እንኳ፣ ጸሎቴን መስማት አልፈለገም።
በጠራሁና በጮኽሁ ጊዜ ጸሎቴ ከለከለ።
ለእርዳታ ጩኸቴን ባሰማም እንኳ አላዳምጥ አለኝ።
እነሆ፥ በዘለፋ እደክማለሁ፤ አልናገርምም፤ አሰምቼም እጮኻለሁ፤ ነገር ግን ፍርድ የለኝም።
ወደ አንተ ጮኽሁ፥ አልሰማኸኝምም፤ እነርሱ ግን ቆመው ተመለከቱኝ።
በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ አሳደገኝ።
ለእስራኤል ሥርዐቱ ነውና፥ የያዕቆብም አምላክ ፍርድ ነውና።
ሳምኬት። በቍጣህ ከደንኸን፤ አሳደድኸንም፤ ገደልኸን፤ አልራራህልንም።
ጸሎታችን እንዳያርግ ራስህን በደመና ከደንህ።
አቤቱ፥ እኔ ስጮኽ የማትሰማው እስከ መቼ ነው? ስለ ግፍ ወደ አንተ እጮኻለሁ፥ አንተም አታድንም።
በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ “ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ?” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህም “አምላኬ አምላኬ፥ ስለ ምን ተውኸኝ?” ማለት ነው።
የሚለምን ሁሉ ይሰጠዋልና፤ የሚፈልግም ያገኛልና፤ ደጅ ለሚመታም ይከፈትለታልና።