ሰቈቃወ 3:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳሌጥ። እንደምትሸምቅ ድብ እንደ ተሸሸገም አንበሳ ሆነብኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሸምቆ እንደ ተኛ ድብ፣ እንደ አደባም አንበሳ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳሌጥ። እንደሚሸምቅ ድብ እንደ ተሸሸገም አንበሳ ሆነብኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ለእኔ እንደሚሸምቅ ድብና እንደ ተደበቀ አንበሳ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳሌጥ። እንደሚሸምቅ ድብ እንደ ተሸሸገም አንበሳ ሆነብኝ። |
በዚያ ወራት እስኪነጋ ድረስ እንደ አንበሳ ታወክሁ፤ እንደዚሁም አጥንቶች ተቀጠቀጡብኝ፤ ከማለዳ ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ተጨነቅሁ።
እኔም ለኤፍሬም እንደ ነብር፥ ለይሁዳም ቤት እንደ አንበሳ ደቦል እሆናለሁና፤ እኔም ነጥቄ እሄዳለሁ፤ እወስድማለሁ፤ የሚያድናቸውም የለም።
በመከራቸው ጊዜ በማለዳ ወደ እኔ ይገሰግሳሉ፤ እንዲህም ይላሉ፥ “ኑ፤ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፤ እርሱ ሰብሮናልና፥ እርሱም ይፈውሰናል፤ እርሱ መትቶናልና፥ እርሱም ይጠግነናል።