አውራጃችንን በእሳት ያቃጥሉ ዘንድ፥ ጐልማሶቻችንንም በጦር ይገድሉ ዘንድ፥ ሕፃኖቻችንንም በምድር ላይ ይፈጠፍጡ ዘንድ፥ ወንዶች ልጆቻችንንና ቆነጃጅቶቻችንን ይማርኩ ዘንድ አዝዘው ነበር።
ኃያላቸው በጐልማሶች እጅ አልወደቀም፤ የቲታንስ ልጆችም አልመቱትም፤ ረጃጅም ግዙፎችም አላጠቁትም፤ የሜራሪ ልጅ ዮዲት ግን በውበቷ ሽባ አደረገችው።