መሳፍንት 8:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የለመነውም የወርቅ ጕትቻ ሚዛኑ ከአምባሩ፥ ከድሪውም፥ የምድያምም ነገሥታት ከለበሱት ከቀዩ ቀሚስ፥ በግመሎቻቸውም አንገት ከነበሩት ሥሉሴዎች ሌላ ሺህ ሰባት መቶ ሰቅለ ወርቅ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌሎቹን ጌጣጌጦች፣ ይኸውም የዐንገት ሐብሉን ከነ እንጥልጥሉ፣ የምድያም ነገሥታት ይለብሱት የነበረውን ሐምራዊ ልብስ ወይም በግመሎቻቸው ዐንገት ላይ ያሉትን ጌጦች ሳይጨምር ጌዴዎን በጠየቃቸው መሠረት የሰጡት የወርቅ ጕትቻ ክብደት ሺሕ ሰባት መቶ ሰቅል ያህል መዘነ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌሎቹን ጌጣ ጌጦች ይኸውም የአንገት ሐብሉን ከነእንጥልጥሉ፥ የምድያም ነገሥታት ይለብሱት የነበረውን ሐምራዊ ልብስ ወይም በግመሎቻቸው አንገት ላይ ያሉትን ጌጦች ሳይጨምር ጌዴዎን በጠየቃቸው መሠረት የሰጡት የወርቅ ጉትቻ ክብደት ሺህ ሰባት መቶ ሰቅል ያህል መዘነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌዴዎን የተቀበለው የጆሮ ጒትቻ ኻያ ኪሎ ያኽል የሚመዝን ሆነ፤ ይህም ሌላውን ጌጣጌጥ፥ የአንገት ሐብልና የምድያማውያን ነገሥታት ይለብሱት የነበረውን ሐምራዊ ልብስ፥ እንዲሁም በግመሎቻቸው አንገት ዙሪያ ያለውን ጌጥ ሳይጨምር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የለመነውም የወርቅ ጉትቻ ሚዛኑ፥ ከአምባሩ፥ ከድሪውም፥ የምድያምም ነገሥታት ከለበሱት ከቀዩ ቀሚስ፥ በግመሎቻቸውም አንገት ከነበሩት ሥሉሴዎች ሌላ፥ ሺህ ሰባት መቶ ሰቅለ ወርቅ ነበረ። |
የሠራተኛና የአንጥረኛ እጅ ሥራ የሆነ ከተርሴስ ጥፍጥፍ ብር፥ ከአፌዝም ወርቅ ይመጣል፤ ልብሳቸውም ሰማያዊና ቀይ ግምጃ ነው፤ ሁሉም የብልሃተኞች ሥራ ናቸው።
ዓላማ እንዲሆንልሽ ሸራሽ ከግብፅ በፍታና ከወርቀ ዘቦ ተሠርቶአል፤ መደረቢያሽም ከኤሊሳ ደሴቶች ሰማያዊና ቀይ ሐር ተሠርቶአል።
ጌታችን ኢየሱስም የእሾህ አክሊል ደፍቶ፥ የቀይ ሐር መጐናጸፊያም ለብሶ ወደ ውጭ ወጣ፤ ጲላጦስም፥ “እነሆ፥ ሰውዬው” አላቸው።
ሴቲቱም በቀይና በሐምራዊ ልብስ ተጐናጽፋ በወርቅና በከበሩ ድንጋዮች በዕንቈችም ተሸልማ ነበር፤ በእጅዋም የሚያስጸይፍ ነገር የዝሙትዋም ርኵሰት የሞላባትን የወርቅ ጽዋ ያዘች፤
ጭነትም ወርቅና ብር፥ የከበረም ድንጋይ ዕንቁም፥ ቀጭንም ተልባ እግር፥ ቀይም ሐር፥ ሐምራዊም ልብስ፥ የሚሸትም እንጨት ሁሉ፥ ከዝሆን ጥርስም የተሠራ ዕቃ ሁሉ፥ እጅግም ከከበረ እንጨት፥ ከናስም ከብረትም ከዕብነ በረድም የተሠራ ዕቃ ሁሉ፥
“በቀጭን ተልባ እግርና በቀይ ሐምራዊም ልብስ ለተጐናጸፈች በወርቅና በከበረ ድንጋይም በዕንቁም ለተሸለመች ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት! ወዮላት! ይህን የሚያህል ታላቅ ባለ ጠግነት በአንድ ሰዓት ጠፍቶአልና፤” እያሉ ስቃይዋን ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ይቆማሉ። የመርከብም መሪ ሁሉ በመርከብም ወደ ማናቸውም ስፍራ የሚሄድ ሁሉ መርከበኞችም ከባሕርም የሚጠቀሙ ሁሉ በሩቅ ቆሙ፤
ዛብሄልና ስልማናም፥ “ኀይልህ እንደ ጐልማሳ ኀይል ነውና አንተ ተነሥተህ ውደቅብን” አሉት። ጌዴዎንም ተነሥቶ ዛብሄልንና ስልማናን ገደለ፤ በግመሎቻቸውም አንገት የነበሩትን ሥሉሴዎች ማረከ።
እነርሱም፥ “መስጠትን ፈቅደን እንሰጥሃለን” ብለው መለሱለት። መጐናጸፊያም አነጠፉ፤ ሰውም ሁሉ የምርኮውን ጕትቻ በዚያ ላይ ጣለ።
ጌዴዎንም ምስል አድርጎ ሠራው፤ በከተማውም በኤፍራታ አኖረው፤ እስራኤልም ሁሉ ተከትሎ አመነዘረበት፤ ለጌዴዎንና ለቤቱም ወጥመድ ሆነ።