መሳፍንት 7:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም አሁን እንግዲህ፥ “የፈራ፥ የደነገጠም ከገለዓድ ተራራ ተነሥቶ ይመለስ ብለህ በሕዝቡ ጆሮ አውጅ” አለው። ከሕዝቡም ሃያ ሁለት ሺህ ተመለሱ፤ ዐሥርም ሺህ ቀሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘ማንም የፈራ ቢኖር የገለዓድን ተራራ ትቶ ወደ መጣበት ይመለስ’ ብለህ ለሕዝቡ ዐውጅ።” ስለዚህ ሃያ ሁለቱ ሺሕ ሲመለሱ ዐሥሩ ሺሕ ብቻ ቀሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም እንግዲህ፦ የፈራ የደነገጠም ከገለዓድ ተራራ ተነሥቶ ይመለስ ብለህ በሕዝቡ ጆሮ አውጅ አለው። ከሕዝቡም ሀያ ሁለት ሺህ ተመለሱ፥ ዐሥርም ሺህ ቀሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ለሕዝቡ ‘ከመካከላችሁ ፈሪና ድንጉጥ የሆነ ሰው ካለ ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ፤ እኛም በዚህ በገለዓድ ተራራ ላይ እንቈያለን’ ብለህ ንገራቸው።” በዚህ ምክንያት ኻያ ሁለቱ ሺህ ሲመለሱ ዐሥሩ ሺህ ቀሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም እንግዲህ፦ የፈራ የደነገጠም ከገለዓድ ተራራ ተነሥቶ ይመለስ ብለህ በሕዝቡ ጆሮ አውጅ አለው። ከሕዝቡም ሀያ ሁለት ሺህ ተመለሱ፥ አሥርም ሺህ ቀሩ። |
ጸሐፍቱም ደግሞ ጨምረው፦ ማንም ፈሪና ልበ ድንጉጥ ሰው ቢሆን የወንድሞቹን ልብ እንደ እርሱ እንዳያስፈራ ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ ብለው ለሕዝቡ ይናገሩ።
እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፤ ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ።”
ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።”
ወደ ምናሴም ነገድ ሁሉ መልእክተኞችን ላከ፤ እርሱም ከኋላው ሆኖ ጮኸ፤ መልእክተኞችንም ወደ አሴርና ወደ ዛብሎን ወደ ንፍታሌምም ላከ፤ እነርሱም ሊቀበሉአቸው ወጡ።