Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 7:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጌዴ​ዎ​ንን፥ “ሕዝቡ ገና ብዙ ነው፤ ወደ ውኃ አው​ር​ዳ​ቸው፤ በዚ​ያም እፈ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እኔም፦ ይህ ከአ​ንተ ጋር ይሂድ የም​ለው እርሱ ከአ​ንተ ጋር ይሄ​ዳል፤ እኔም፦ ይህ ከአ​ንተ ጋር አይ​ሂድ የም​ለው እርሱ አይ​ሄ​ድም” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እግዚአብሔር ጌዴዎንን እንዲህ አለው፤ “አሁንም ሰዎቹ ብዙ ናቸው፤ ወደ ወንዝ ይዘሃቸው ውረድ፤ በዚያም እለይልሃለሁ። ‘ይህ ከአንተ ጋራ ይሂድ’ የምለው፣ ከአንተ ጋራ ይሄዳል፤ ነገር ግን፣ ‘ይህ ከአንተ ጋራ አይሂድ’ የምለው፣ ከአንተ ጋራ አይሄድም።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ጌታ ጌዴዎንን እንዲህ አለው፥ “አሁንም ሰዎቹ ብዙ ናቸው፤ ወደ ወንዝ ይዘሃቸው ውረድ፤ በዚያም እጸልይልሃለሁ። ‘ይህ ከአንተ ጋር ይሂድ’ የምለው፥ ከአንተ ጋር ይሄዳል፤ ነገር ግን፥ ‘ይህ ከአንተ ጋር አይሂድ’ የምለው፥ ከአንተ ጋር አይሄድም።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ጌዴዎንን እንዲህ አለው፦ “አሁንም ገና ብዙ ሠራዊት አሉህ፤ እነርሱን ወደ ወንዝ ውሰዳቸውና በዚያ እኔ እፈትናቸዋለሁ፤ ከአንተ ጋር ይሂድ የምለው ሰው ይሂድ፤ ይቅር የምለው ሰው ደግሞ ይመለስ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እግዚአብሔርም ጌዴዎንን፦ ሕዝቡ ገና ብዙ ነው፥ ወደ ውኃ አውርዳቸው፥ በዚያም እፈትናቸዋለሁ፥ እኔም፦ ይህ ከአንተ ጋር ይሂድ የምለው እርሱ ከአንተ ጋር ይሄዳል፥ እኔም፦ ይህ ከአንተ ጋር አይሂድ የምለው እርሱ አይሄድም አለው።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 7:4
10 Referencias Cruzadas  

ከእ​ነ​ዚ​ህም ነገ​ሮች በኋላ እን​ዲህ ሆነ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ​ር​ሃ​ምን ፈተ​ነው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “አብ​ር​ሃም! አብ​ር​ሃም ሆይ፥” እር​ሱም፥ “እነሆ፥ አለሁ” አለ።


መን​ገ​ዴን ፈጽሞ ዐወቀ፥ እንደ ወር​ቅም ፈተ​ነኝ


መታ​ሰ​ቢ​ያ​ቸ​ውን ከም​ድር ያጠፋ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉን በሚ​ያ​ደ​ርጉ ላይ ነው።


የኃ​ጥ​ኣን ክፋት ያል​ቃል፥ ጻድ​ቃ​ንን ግን ታቃ​ና​ቸ​ዋ​ለህ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቡ​ና​ንና ኵላ​ሊ​ትን ይመ​ረ​ም​ራል።


ሕዝ​ቡ​ንም ወደ ውኃ አወ​ረደ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጌዴ​ዎ​ንን፥ “ውሻ እን​ደ​ሚ​ጠጣ ውኃ በም​ላሱ የሚ​ጠ​ጣ​ውን ሁሉ፥ እር​ሱን ለብ​ቻው አድ​ር​ገው፤ እን​ዲ​ሁም ሊጠጣ በጕ​ል​በቱ የሚ​ን​በ​ረ​ከ​ከ​ውን ሁሉ ለብ​ቻው አድ​ር​ገው” አለው።


ዮና​ታ​ንም ጋሻ ጃግ​ሬ​ውን፥ “ና፥ ወደ እነ​ዚህ ቈላ​ፋን ሰፈር እን​ለፍ፤ በብዙ ወይም በጥ​ቂት ማዳን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አያ​ስ​ቸ​ግ​ረ​ው​ምና ምና​ል​ባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይረ​ዳን ይሆ​ናል” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ፊቱን፥ የቁ​መ​ቱ​ንም ዘለ​ግታ አትይ፤ ሰው እን​ደ​ሚ​ያይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አያ​ይ​ምና ናቅ​ሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ልብን ያያል” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos