ካህናቱና ነቢያተ ሐሰትም ለአለቆቹና ለሕዝቡ ሁሉ፥ “በጆሮአችሁ እንደ ሰማችሁ በዚች ከተማ ላይ ትንቢት ተናግሮአልና ይህ ሰው ሞት የሚገባው ነው” ብለው ተናገሩ።
መሳፍንት 6:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የከተማዉም ሰዎች ኢዮአስን፥ “የበዓልን መሠዊያ አፍርሶአልና፥ በዙሪያውም ያለውን የማምለኪያ ዐጸድ ቈርጦአልና ይገደል ዘንድ ልጅህን አምጣ” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የከተማዪቱም ሰዎች ኢዮአስን፣ “የበኣልን መሠዊያ ያፈረሰና በአጠገቡ የቆመውን የአሼራን ምስል ዐምድ የሰበረው ልጅህ በመሆኑ መሞት ስላለበት አውጣልን አሉት።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የከተማይቱም ሰዎች ኢዮአስን፥ “የበኣልን መሠዊያ ያፈረሰና በአጠገቡ የቆመውን የአሼራን ምስል ዐምድ የሰበረው ልጅህ በመሆኑ መሞት ስላለበት አውጣልን አሉት።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ኢዮአስን “የባዓልን መሠዊያ ስላፈረሰና በአጠገቡ ያለውንም የአሼራን ምስል ሰባብሮ ስለ ጣለ፥ እንዲሞት ልጅህን ወዲህ አውጣልን!” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የከተማውም ሰዎች ኢዮአስን፦ የበኣልን መሠዊያ አፍርሶአልና፥ በዙሪያውም ያለውን የማምለኪያ ዐፀድ ቈርጦአልና እንዲሞት ልጅህን አውጣ አሉት። |
ካህናቱና ነቢያተ ሐሰትም ለአለቆቹና ለሕዝቡ ሁሉ፥ “በጆሮአችሁ እንደ ሰማችሁ በዚች ከተማ ላይ ትንቢት ተናግሮአልና ይህ ሰው ሞት የሚገባው ነው” ብለው ተናገሩ።
እርስዋ የተቀረጹ ምስሎች ምድር ናትና፥ እነርሱም በደሴቶችዋ ይመካሉና ሰይፍ በውኆችዋ ላይ አለ፤ እነርሱም ይደርቃሉ።
ከምኵራባቸው ያስወጡአችኋል፤ ደግሞም እናንተን የሚገድላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር አገልግሎት የሚያቀርብ የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል።
እርስ በርሳቸውም፥ “ይህን ነገር ያደረገ ማን ነው?” ተባባሉ። በጠየቁና በመረመሩም ጊዜ፥ “ይህን ነገር ያደረገ የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን ነው” አሉ።
ኢዮአስም በእርሱ ላይ የተነሡበትን ሁሉ፥ “ለበዓል እናንተ ዛሬ ትበቀሉለታላችሁን? ወይስ የበደለውን ትገድሉለት ዘንድ የምታድኑት እናንተ ናችሁን? እርሱ አምላክ ከሆነስ የበደለው እስከ ነገ ድረስ ይሙት። መሠዊያዉንም ያፈረሰውን እርሱ ይበቀለው” አላቸው።