መሳፍንት 5:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በነጫጭ አህዮች ላይ የምትጫኑ፥ በፍርድ ወንበር ላይየምትቀመጡ፥ በመንገድም የምትሄዱ በቃላችሁ ተናገሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እናንተ በነጫጭ አህዮች የምትጋልቡ፣ በባለ ግላስ ኮርቻ ላይ የምትቀመጡ፣ በመንገድ ላይ የምትጓዙ፣ በውሃ ምንጮች ዙሪያ ያለውን፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በነጫጭ አህዮች ላይ የምትጫኑ፥ በወላንሳ ላይ የምትቀመጡ፥ በመንገድም የምትሄዱ፥ ተናገሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ኮርቻ በተጫኑ በነጫጭ አህዮች ላይ ተቀምጣችሁ የምትጓዙ፥ እናንተ በምቹና በአማረ ግላስ ላይ የምትንደላቀቁ፥ እናንተ በእግር የምትንሸራሸሩ፥ ስለዚህ ነገር ተናገሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በነጫጭ አህዮች ላይ የምትጫኑ፥ በወላንሳ ላይ የምትቀመጡ፥ በመንገድም የምትሄዱ፥ ተናገሩ። |
በሠላሳ ሁለት የአህያ ግልገሎች ይቀመጡ የነበሩ ሠላሳ ሁለት ልጆችም ነበሩት፤ ለእነርሱም እስከ ዛሬ ድረስ የኢያዕር መንደሮች የተባሉ በገለዓድ ምድር ያሉ ሠላሳ ሁለት ከተሞች ነበሩአቸው።
አርባም ልጆች፥ ሠላሳም የልጅ ልጆች ተወለዱለት፤ በሰባም የአህያ ግልገሎች ላይ ይቀመጡ ነበር። እስራኤልንም ስምንት ዓመት ገዛ።