ሎጥም ወጣ፤ ልጆቹን ለሚያገቡት ለአማቾቹም አላቸው፥ “ተነሡ፤ ከዚች ስፍራ ውጡ፤ እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ያጠፋታልና።” ለአማቾቹ ግን የሚያፌዝባቸው መሰላቸው።
መሳፍንት 4:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዲቦራም ባርቅን፥ “እግዚአብሔር ሲሣራን በእጅህ አሳልፎ የሚሰጥበት ቀን ዛሬ ነውና ተነሣ፤ እነሆ፥ እግዚአብሔር በፊትህ ይሄዳል” አለችው። ባርቅም ዐሥር ሺህ ሰዎች ተከትለውት ከታቦር ተራራ ወረደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ዲቦራ ባርቅን፣ “ተነሣ! እግዚአብሔር ሲሣራን በእጅህ አሳልፎ የሰጠባት ቀን ይህች ናት፤ እነሆ እግዚአብሔር በፊትህ ቀድሞ ወጥቷል” አለችው። ስለዚህ ባራቅ ዐሥር ሺሕ ሰዎችን አስከትሎ ከታቦር ተራራ ወረደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ጊዜ ዲቦራ ባራቅን፥ “ተነሣ! ጌታ ሲሣራን በእጅህ አሳልፎ የሰጠባት ቀን ይህች ናት፤ እነሆ ጌታ በፊትህ ቀድሞ ወጥቶአል” አለችው። ስለዚህ ባራቅ ዐሥር ሺህ ሰዎችን አስከትሎ ከታቦር ተራራ ወረደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዲቦራም ባራቅን “እግዚአብሔር አንተን በሲሣራ ላይ ድልን እንድትቀዳጅ የሚያደርግበት ቀን ዛሬ ስለ ሆነ ተነሥ! እነሆ! እግዚአብሔር ይመራሃል” አለችው፤ ባራቅም ዐሥር ሺህ ወታደሮች ተከትለውት ከታቦር ተራራ ወረደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዲቦራም ባርቅን፦ እግዚአብሔር ሲሣራን በእጅህ አሳልፎ የሚሰጥበት ቀን ዛሬ ነውና ተነሣ፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር በፊትህ ወጥቶአል አለችው። ባርቅም አሥር ሺህ ሰዎች ተከትለውት ከታቦር ተራራ ወረደ። |
ሎጥም ወጣ፤ ልጆቹን ለሚያገቡት ለአማቾቹም አላቸው፥ “ተነሡ፤ ከዚች ስፍራ ውጡ፤ እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ያጠፋታልና።” ለአማቾቹ ግን የሚያፌዝባቸው መሰላቸው።
ከከተማዪቱም ወጥተው ገና ሳይርቁ ዮሴፍ ለቤቱ አዛዥ እንዲህ አለ፥ “ተነሥተህ ሰዎቹን ተከትለህ ያዛቸው፤ እንዲህም በላቸው፦ በመልካሙ ፈንታ ስለምን ክፉን መለሳችሁ?
በሾላውም ዛፍ ራስ ውስጥ የሽውሽውታ ድምፅ ስትሰማ፥ በዚያ ጊዜ እግዚአብሔር የፍልስጥኤማውያንን ጭፍራ ለመምታት በፊትህ ወጥቶ ይሆናልና በዚያ ጊዜ ፍጠን” አለው።
እግዚአብሔር በፊታችሁ ይሄዳልና፥ የእስራኤልም አምላክ ይሰበስባችኋልና በችኮላ አትወጡም፤ በመኮብለልም አትሄዱም።
ሰባሪው በፊታቸው ወጥቶአል፥ እነርሱም ሰብረው ወደ በሩ አልፈዋል፥ በእርሱም በኩል ወጥተዋል፥ ንጉሣቸውም በፊታቸው አልፎአል፥ እግዚአብሔርም በራሳቸው ላይ ነው።
አምላክህም እግዚአብሔር በፊትህ እንዲያልፍ ዛሬ ዕወቅ፤ እርሱ የሚበላ እሳት ነው፤ እርሱ ያጠፋቸዋል፤ በፊትህም ያዋርዳቸዋል፤ እግዚአብሔርም እንደ ነገረህ ከፊትህ ያርቃቸዋል፥ ፈጥኖም ያጠፋቸዋል።
እግዚአብሔርም ኢያሱን፥ “በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼአቸዋለሁና አትፍራቸው፤ ከእነርሱም አንድ ሰው በፊትህ የሚተርፍ የለም፤” አለው።
ተነሣና ሕዝቡን ቀድስ እንዲህም በላቸው፦ ‘እስራኤል ሆይ! እርም የሆነ ነገር በመካከልህ አለ፤ እርምም የሆነውን ነገር ከመካከላችሁ እስክታጠፉ ድረስ በጠላቶቻችሁ ፊት መቆም አትችሉም’ ብሎ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ተናግሮአልና እስከ ነገ ራሳችሁን አንጹ።
እርሱም፥ “ተነሺ እንሂድ” አላት፤ እርስዋ ግን ሞታ ነበርና አልመለሰችም፤ በዚያ ጊዜም በአህያው ላይ ጫናት፤ ተነሥቶም ወደ ስፍራው ተመለሰ።
ማልደውም ተነሡ፤ በነጋም ጊዜ ሳሙኤል ሳኦልን፥ “ከሰገነቱ ላይ ጠርቶ፦ ተነሣና ላሰናብትህ” አለው። ሳኦልም ተነሣ፤ እርሱና ሳሙኤልም ሁለቱ ወደ ሜዳ ወጡ።