የያዕቆብም ልጆች ከምድረ በዳ መጡ፤ ይህንም በሰሙ ጊዜ ፈጽመው ደነገጡ፤ የያዕቆብን ልጅ በመተኛቱ በእስራኤል ላይ ኀፍረትን ስላደረገ አዘኑ፤ እጅግም ተቈጡ፤ እንዲህ አይደረግምና።
መሳፍንት 20:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም ዕቅብቴን ይዤ በመለያያዋ ቈራረጥኋት፤ በእስራኤልም ዘንድ እንደዚህ ያለ ስንፍና ስለ ሠሩ ወደ እስራኤል ርስት አውራጃ ሁሉ ሰደድሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቁባቴንም ሬሳ ከቈራረጥሁ በኋላ እያንዳንዱን ቍራጭ፣ እያንዳንዱ የእስራኤል ርስት ወዳለበት አገር ሰደድሁ፤ ይህን ያደረግሁትም ሰዎቹ በእስራኤል ዘንድ አሠቃቂና አስነዋሪ ድርጊት ስለ ፈጸሙ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቁባቴንም ሬሳ ከቈራረጥሁ በኋላ እያንዳንዱን ቁራጭ፥ እያንዳንዱ የእስራኤል ርስት ወዳለበት አገር ሰደድሁ፤ ይህን ያደረግሁትም ሰዎቹ በእስራኤል ዘንድ አሠቃቂና አስነዋሪ ድርጊት ስለፈጸሙ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ የቁባቴን አስከሬን ወስጄ ቈራረጥሁት፤ እነርሱ ይህን የመሰለ ክፉ በደል ስለ ሠሩ የቈራረጥኋቸውን ቊርጥራጮች ወደ እስራኤል አገር ሁሉ ላክሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም ቁባቴን ይዤ ቈራረጥኋት፥ በእስራኤልም ዘንድ እንደዚህ ያለ ኃጢአትና ስንፍና ስለ ተሠራ ወደ እስራኤል ርስት አገር ሁሉ ሰደድሁ። |
የያዕቆብም ልጆች ከምድረ በዳ መጡ፤ ይህንም በሰሙ ጊዜ ፈጽመው ደነገጡ፤ የያዕቆብን ልጅ በመተኛቱ በእስራኤል ላይ ኀፍረትን ስላደረገ አዘኑ፤ እጅግም ተቈጡ፤ እንዲህ አይደረግምና።
ስለዚህ ከእናንተ በፊት የነበሩ ሰዎች የሠሩትን ጸያፍ የሆነውን ወግ ሁሉ እንዳትሠሩ፥ በእርሱም እንዳትረክሱ ሥርዐቴን ጠብቁ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና።”
ምልክት የታየበት ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን አፍርሶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ በደል አድርጎአልና፥ እርሱና ያለው ሁሉ በእሳት ይቃጠላሉ።”
ሰውነታቸውንም ደስ ባሰኙ ጊዜ የኃጥኣን ልጆች የሆኑ የከተማው ሰዎች ቤቱን ከበቡ፤ በሩንም ይደበድቡ ነበር፤ ባለቤቱንም ሽማግሌውን ሰው፥ “ወደ ቤትህ የገባውን ሰው እንድንደርስበት አውጣልን” አሉት።
ባለቤቱም ሽማግሌው ወደ እነርሱ ወጥቶ፥ “ወንድሞቼ ሆይ! ይህን ክፉ ነገር ታደርጉ ዘንድ አይገባችሁም፤ ይህ ሰው ወደ ቤቴ ከገባ በኋላ እንደዚህ ያለ ስንፍና አትሥሩ።
ወደ ቤቱም በገባ ጊዜ ካራ አነሣ፤ ዕቅብቱንም ይዞ ከአጥንቶችዋ መለያያ ላይ ለዐሥራ ሁለት ቈራርጦ ወደ እስራኤል ሀገር ሁሉ ሰደደ።
በእስራኤል ላይ ስላደረጉት ስንፍና ሁሉ የብንያም ገባዖንን ይወጉ ዘንድ ለሚሄዱ ሕዝብ በመንገድ ስንቅ የሚይዙ ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ከመቶው ዐሥር ሰው፥ ከሺሁም መቶ ሰው፥ ከዐሥሩም ሺህ አንድ ሺህ ሰው እንወስዳለን።”