ነቢያትም ሁሉ እንዲህ ብለው ትንቢት ተናገሩ፥ “ወደ ሬማት ዘገለዓድ ዝመት፤ እግዚአብሔርም ይረዳሃል። ሶርያውያንንና ንጉሣቸውንም በእጅህ አሳልፎ ይሰጣቸዋል።”
መሳፍንት 18:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያም ካህን፥ “የምትሄዱበት መንገድ በእግዚአብሔር ፊት ነውና በሰላም ሂዱ” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑም፣ “በሰላም ሂዱ፤ መንገዳችሁን እግዚአብሔር አቃንቶላችኋል” ብሎ መለሰላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም፥ “የምትሄዱበት መንገድ በጌታ ፊት ነውና በሰላም ሂዱ” ብሎ መለሰላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑም፦ “ሂዱ በጒዞአችሁ ምንም ችግር አይገጥማችሁም፥ እግዚአብሔር ይጠብቃችኋል” ሲል መለሰላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ የምትሄዱበት መንገድ በእግዚአብሔር ፊት ነውና በደኅና ሂዱ አላቸው። |
ነቢያትም ሁሉ እንዲህ ብለው ትንቢት ተናገሩ፥ “ወደ ሬማት ዘገለዓድ ዝመት፤ እግዚአብሔርም ይረዳሃል። ሶርያውያንንና ንጉሣቸውንም በእጅህ አሳልፎ ይሰጣቸዋል።”
ወደ ንጉሡም ደረሰ። ንጉሡም፥ “ሚክያስ ሆይ! ወደ ሬማት ዘገለዓድ ለሰልፍ እንሂድን? ወይስ እንቅር?” አለው። እርሱም፥ “ውጣና ተከናወን፤ እግዚአብሔርም በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታል” ብሎ መለሰለት።
የእስራኤልም ንጉሥ ነቢያቱን አራት መቶ የሚያህሉትን ሰዎች ሰበሰበ፤ የእስራኤል ንጉሥም፥ “ወደ ሬማት ዘገለዓድ ለሰልፍ ልሂድን? ወይስ ልቅር?” አላቸው። እነርሱም፥ “እግዚአብሔር በንጉሥ እጅ አሳልፎ ይሰጣታልና ውጣ” አሉት።
ሙሴም ሄደ፤ ወደ አማቱ ወደ ዮቶርም ተመለሰ፥ “እስከ ዛሬ በሕይወት እንደ አሉ አይ ዘንድ ተመልሼ ወደ ግብፅ ወደ ወንድሞች እሄዳለሁ” አለው። ዮቶርም ሙሴን፥ “በደኅና ሂድ” አለው።
እነሆ ሐሰትን በሚያልሙ፥ በሚናገሩም፥ በሐሰታቸውና በድፍረታቸውም ሕዝቤን በሚያስቱ በነቢያት ላይ ነኝ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ እኔም አልላክኋቸውም፤ አላዘዝኋቸውምም፤ ለእነዚህ ሕዝብ በማናቸውም አይረቡአቸውም፥” ይላል እግዚአብሔር።
አምላክህ እግዚአብሔር የሚጐበኛት ሀገር ናት፤ ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ የአምላክህ የእግዚአብሔር ዐይን ሁል ጊዜ በእርስዋ ላይ ነው።
አምስቱም ሰዎች ሄዱ፤ ወደ ሌሳም ደረሱ፤ በውስጡም የነበሩትን ሕዝብ ተዘልለው አዩአቸው፤ እንደ ሲዶናውያንም ልማድ ጸጥ ብለው፥ ዐርፈው፥ ተዘልለውም ተቀምጠው ነበር፤ በተመዘገበች የርስታቸው ምድርም ቃልን መናገር አልቻሉም፤ ከሲዶናውያንም ርቀው ይኖሩ ነበር። ከሶርያውያንም ጋር ግንኙነት አልነበራቸውም።