እግዚአብሔርም ለዳዊትና ለልጁ ለሰሎሞን፥ “በዚህ ቤትና ከእስራኤል ነገድ ሁሉ በመረጥኋት በኢየሩሳሌም ስሜን ለዘለዓለም አኖራለሁ፤
መሳፍንት 17:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንዱን ሺህ አንድ መቶ ብርም ለእናቱ መለሰላት፤ እናቱም፥ “ይህን ብር የተቀረፀ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ምስል አድርጌ ከእጄ ስለ ልጄ ለእግዚአብሔር እቀድሰዋለሁ፤ አሁንም ለአንተ እመልሰዋለሁ” አለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ሺሕ አንድ መቶውን ሰቅል ብር በመለሰላት ጊዜ እናቱ፣ “ብሬን የተቀረጸ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ጣዖት ለማበጀት ስለ ልጄ ለእግዚአብሔር እቀድሰዋለሁ፤ አሁንም ለአንተው መልሼ እሰጥሃለሁ” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ ሺህ አንድ መቶውን ሰቅል ብር በመለሰላት ጊዜ፥ እናቱ “ብሬን የተቀረጸ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ጣዖት ለማበጀት ስለ ልጄን ለጌታ እቀድሰዋለሁ፤ አሁንም ለአንተው መልሼ እሰጥሃለሁ” አለችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጁም ገንዘቡን መልሶ ለእናቱ ሰጣት፤ እርስዋም “እኔ ራሴ ብሩን ለእግዚአብሔር ስለ ልጄ የተለየ አደርገዋለሁ፤ ከእንጨት ተሠርቶ በብር የተለበጠ ጣዖት ማሠሪያም ይሆናል፤ ስለዚህ ብሩን ለአንተ መልሼ እሰጥሃለሁ” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንዱን ሺህ እንዱን መቶ ብርም መለሰላት፥ እናቱም፦ ይህን ብር የተቀረጸ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ምስል አድርጌ ከእጄ ስለ ልጄ ለእግዚአብሔር እቀድሰዋለሁ፥ አሁንም ለአንተ እመልሰዋለሁ አለች። |
እግዚአብሔርም ለዳዊትና ለልጁ ለሰሎሞን፥ “በዚህ ቤትና ከእስራኤል ነገድ ሁሉ በመረጥኋት በኢየሩሳሌም ስሜን ለዘለዓለም አኖራለሁ፤
የብር አማልክትን አታምልኩ፤ የወርቅ አማልክትንም አታምልኩ። የዕንጨትና የድንጋይ አምላክንም አታምልኩ፤ እንዲህ ያለ አምላክን ለእናንተ አታድርጉ።
“በላይ በሰማይ ከአለው፥ በታችም በምድር ከአለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ከአለው ነገር የማናቸውንም ምስል ለአንተ አምላክ አታድርግ።
በብርም ወደ ተለበጡ፥ በወርቅም ወደ አጌጡ ወደ ጣዖታቱ እንሂድ የሚሉ ናቸው፤ ያንጊዜ እንደ ትቢያ የደቀቁ ይሆናሉ፤ እንደ ውኃም ይደፈርሳሉ፤ በእነርሱም ጥራጊዎችን ይጥሉባቸዋል።
በሬን የሚሠዋልኝ ኃጥእ ውሻን እንደሚያርድልኝ ነው፤ የእህልን ቍርባን የሚያቀርብም የእሪያን ደም እንደሚያቀርብ ነው፤ ዕጣንንም ለመታሰቢያ የሚያጥን አምላክን እንደሚፀርፍ ነው፤ እነዚህ የገዛ መንገዳቸውን መረጡ፤ ነፍሳቸውም በርኵሰታቸው ደስ ይላታል።
ጣዖታትንም አትከተሉ፤ ቀልጠው የተሠሩትንም የአማልክት ምስሎች ለእናንተ አታድርጉ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።
ከምኵራባቸው ያስወጡአችኋል፤ ደግሞም እናንተን የሚገድላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር አገልግሎት የሚያቀርብ የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል።
መሠዊያቸውንም አፍርሱ፤ ሐውልቶቻቸውንም ሰባብሩ፤ የማምለኪያ ዐጸዶቻቸውንም ቁረጡ፤ የአማልክቶቻቸውንም ምስሎች በእሳት አቃጥሉ፤ ከዚያም ስፍራ ስማቸውን አጥፉ።
“በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ የሠራተኛ እጅ ሥራን፥ የተቀረፀ ወይም ቀልጦ የተሠራ ምስልን የሚያደርግ፥ በስውርም የሚያቆመው ሰው ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ መልሰው አሜን ይላሉ።
እናቱንም፥ “ከአንቺ ዘንድ የተሰረቀው፥ የረገምሽበትም፥ በጆሮዬም የተናገርሽበት አንድ ሺህ አንድ መቶ ብር እነሆ፥ በእኔ ዘንድ አለ፤ እኔም ወስጄው ነበር” አላት። እናቱም፥ “ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔር ይባርክህ” አለችው።
ለእናቱም ገንዘቡን መለሰላት እናቱም ብሩን ወስዳ ከእርሱ ሁለቱን መቶ ብር ለአንጥረኛ ሰጠችው፤ እርሱም የተቀረፀ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ምስል አደረገው። በሚካም ቤት አስቀመጡት።
የዳንም ልጆች የተቀረፀውን የሚካን ምስል ለራሳቸው አቆሙ፤ የሙሴም ልጅ የጌርሳም ልጅ ዮናታን፥ እርሱና ልጆቹ እስከ ሀገራቸው ምርኮ ድረስ ለዳን ነገድ ካህናት ነበሩ።