ንጉሡም ሰሎሞን ሴቶችን ይወድ ነበር፥ ከባዕዳን ሕዝብም የፈርዖንን ልጅ፥ ሞዓባውያትንና አሞናውያትን፥ ሶርያውያትንና ሲዶናውያትን፥ ኤዶማውያትንና አሞሬዎናውያትንም፥ ኬጤዎናውያትንም፦ ሚስቶችን አገባ።
መሳፍንት 16:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህ በኋላ በሶሬሕ ሸለቆ የነበረች ደሊላ የተባለች አንዲት ሴትን ወደደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከጥቂት ጊዜ በኋላ ሳምሶን በሶሬቅ ሸለቆ የምትኖር ደሊላ የምትባል አንዲት ሴት ወደደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጊዜ በኋላ ሳምሶን በሶሬቅ ሸለቆ የምትኖር ደሊላ የምትባል አንዲት ሴት ወደደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሶምሶን በሶሬቅ ሸለቆ የምትኖር ደሊላ ተብላ የምትጠራ አንዲት ሴት ወደደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህም በኋላ በሶሬቅ ሸለቆ የነበረች ደሊላ የተባለች አንዲት ሴትን ወደደ። |
ንጉሡም ሰሎሞን ሴቶችን ይወድ ነበር፥ ከባዕዳን ሕዝብም የፈርዖንን ልጅ፥ ሞዓባውያትንና አሞናውያትን፥ ሶርያውያትንና ሲዶናውያትን፥ ኤዶማውያትንና አሞሬዎናውያትንም፥ ኬጤዎናውያትንም፦ ሚስቶችን አገባ።
የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን በዚህ ነገር ኀጢአት አድርጎ የለምን? በብዙ አሕዛብም መካከል እንደ እርሱ ያለ ንጉሥ አልነበረም፤ በአምላኩም ዘንድ የተወደደ ነበረ፤ እግዚአብሔርም በእስራኤል ሁሉ ላይ አንግሦት ነበር፤ እርሱንም እንኳ እንግዶች ሴቶች አሳቱት።
የዐመፀኛ አፍ ጥልቅ ጕድጓድ ነው፤ በእግዚአብሔርም ዘንድ የተጠላ በእርሱ ውስጥ ይወድቃል። በሰው ፊት ክፉዎች መንገዶች አሉ፥ ከእነርሱም ይርቅ ዘንድ አይወድድም። ከክፉና ከጠማማ መንገድም መራቅ አግባብ ነው።
ሶምሶንም እስከ እኩለ ሌሊት ተኛ፤ በእኩለ ሌሊትም ተነሥቶ የከተማዪቱን በር መዝጊያ ያዘ፤ ከሁለቱ መቃኖችና ከመወርወሪያው ጋር ነቀለው፤ በትከሻውም ላይ አደረገ፤ በኬብሮንም ፊት ወዳለው ተራራ ራስ ላይ ተሸክሞት ወጣ፤ በዚያም ጣለው።
የፍልስጥኤማውያን መሳፍንትም ወደ እርስዋ ወጥተው፥ “እርሱን አባብለሽ በእርሱ ያለ ታላቅ ኀይል በምን እንደ ሆነ፥ እኛም እርሱን ለማዋረድ እናስረው ዘንድ የምናሸንፈው በምን እንደ ሆነ ዕወቂ፤ እኛም እያንዳንዳችን ሺህ አንድ መቶ ብር እንሰጥሻለን” አሉአት።