መሳፍንት 15:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሶምሶንም ጭን ጭናቸውን ብሎ በታላቅ አገዳደል መታቸው፤ ወርዶም ኢጣም በምትባል ዋሻ በወንዝ ዳር ተቀመጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉኛ መታቸው፤ ከእነርሱም ብዙዎችን ገደለ፤ ከዚያም ወርዶ በኤጣም ዐለት ዋሻ ተቀመጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉኛ መታቸው፤ ከነርሱም ብዙዎችን ገደለ፤ ከዚያም ወርዶ በኢታም ዐለት ዋሻ ተቀመጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወዲያውም ብርቱ አደጋ ጥሎባቸው ከእነርሱ ብዙዎችን ገደለ፤ ከዚህም በኋላ ሄዶ ዔጣም ተብላ በምትጠራ ስፍራ በዋሻ ውስጥ ተቀመጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ጭን ጭናቸውን ብሎ በታላቅ አገዳደል መታቸው፥ ወርዶም በኤጣም ዓለት ባለው ዋሻ ውስጥ ተቀመጠ። |
እግዚአብሔር በዚህ ተራራ ላይ ዕረፍትን ይሰጠናል፤ እህልም በመንኰራኵር ጭድም በጭቃ እንደሚበራይ እንዲሁ ሞዓብ ይረገጣል።
መጭመቂያውን ብቻዬን ረግጫለሁ፤ ከአሕዛብም አንድ ሰው ከእኔ ጋር አልነበረም፤ በቍጣዬም ረገጥኋቸው፤ በመዓቴም ወደ መሬት ጣልጥህዋቸው፤ ደማቸውንም በምድር ላይ አፈሰስሁ፤ ልብሴም ሁሉ በደም ታለለ።
የእሳት ኀይልን አጠፉ፤ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፤ ከድካማቸው በረቱ፤ በጦርነት ኀይለኞች ሆኑ፤ የባዕድ ጭፍሮችንም አባረሩ።
የይሁዳም ሰዎች ሁሉ፥ “በእኛ ላይ የወጣችሁት ለምንድን ነው?” አሉ። እነርሱም፥ “ሶምሶንን ልናስር፥ እንዳደረገብንም ልናደርግበት መጥተናል” አሏቸው።
ከይሁዳም ሰዎች ሦስት ሺህ የሚያህሉ በኢጣም ዓለት ወዳለው ዋሻ ወርደው ሶምሶንን፥ “ገዢዎቻችን ፍልስጥኤማውያን እንደሆኑ አታውቅምን? ያደረግህብን ይህ ምንድን ነው?” አሉት። ሶምሶንም፥ “እንዳደረጉባችሁ እንዲሁ አደረግሁባቸው” አላቸው።
ሶምሶንም አላቸው- “ይህን ብታደርጉም ደስ አይለኝም፤ በቀሌ ከአንድ ሰው ብቻ አይደለም፤ ሁላችሁንም እበቀላችኋለሁ፤ ከዚያም በኋላ አርፋለሁ።”