Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መሳፍንት 15:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ክፉኛ መታቸው፤ ከነርሱም ብዙዎችን ገደለ፤ ከዚያም ወርዶ በኢታም ዐለት ዋሻ ተቀመጠ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ክፉኛ መታቸው፤ ከእነርሱም ብዙዎችን ገደለ፤ ከዚያም ወርዶ በኤጣም ዐለት ዋሻ ተቀመጠ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ወዲያውም ብርቱ አደጋ ጥሎባቸው ከእነርሱ ብዙዎችን ገደለ፤ ከዚህም በኋላ ሄዶ ዔጣም ተብላ በምትጠራ ስፍራ በዋሻ ውስጥ ተቀመጠ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ሶም​ሶ​ንም ጭን ጭና​ቸ​ውን ብሎ በታ​ላቅ አገ​ዳ​ደል መታ​ቸው፤ ወር​ዶም ኢጣም በም​ት​ባል ዋሻ በወ​ንዝ ዳር ተቀ​መጠ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እርሱም ጭን ጭናቸውን ብሎ በታላቅ አገዳደል መታቸው፥ ወርዶም በኤጣም ዓለት ባለው ዋሻ ውስጥ ተቀመጠ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 15:8
9 Referencias Cruzadas  

በቁጣዬም አሕዛብን ረገጥሁ በመዓቴም ቀጠቀጥኋቸው፥ ደማቸውንም ምድር ላይ አፈሰስኩት።”


“መጥመቂያውን ብቻዬን ረግጫለሁ፥ ከአሕዛብም አንድ ሰው ከእኔ ጋር አልነበረም፤ በቁጣዬ ረገጥኋቸው በመዓቴም ቀጠቀጥኋቸው፤ ደማቸውም በልብሴ ላይ ተረጭቶአል፥ ልብሴንም ሁሉ አሳድፌአለሁ።


የጌታም እጅ በዚህ ተራራ ላይ ታርፋለች፤ ጭድም በጭቃ ውስጥ እንደሚረገጥ እንዲሁ ሞዓብ በሥፍራው ይረገጣል።


የእሳትን ኃይል አጠፉ፤ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፤ ከድካማቸው ብርቱ ሆኑ፤ በጦርነት ኀይለኞች ሆኑ፤ የባዕድ ወራሪዎችን አባረሩ።


ሳምሶንም፥ “እንግዲህ እናንተ ይህን ካደረጋችሁ እኔ ደግሞ ሳልበቀላችሁ አልመለስም” አለ።


ፍልስጥኤማውያን ወጥተው በይሁዳ ሰፈሩ፤ ከዚያም በሌሒ አጠገብ ተበታትነው አደፈጡ።


ከዚያም ሦስት ሺህ ሰዎች ከይሁዳ ተነሥተው በኤታም ዐለት ወዳለው ዋሻ ወርደው ሳምሶንን፥ “ፍልስጥኤማውያን ገዦቻችን መሆናቸውን አታውቅምን? ያደረግህብንስ ነገር ምንድነው?” ብለው ጠየቁት። ሳምሶንም፥ “ያደረግሁት እነርሱ ያደረ ጉብኝን ነው” በማለት መለሰላቸው።


የይሁዳም ሰዎች፥ “ልትወጉን የመጣችሁት ለምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቋቸው። እነርሱም “እኛ የመጣነው ሳምሶንን ልና ስርና ያደረገብንን ልናደርግበት ነው” ብለው መለሱላቸው።


እርሱም ቤተ ልሔምን፥ ኤጣምን፥ ቴቁሔን ቆረቆረ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios