ሐሰትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል፥ የሥራውንም መቅሠፍት ይፈጽማል። እግዚአብሔር ደስ ብሎት የሚሰጥ ሰውን ይወድዳል፥ ከንቱ ሥራውን ግን ይጠላል።
መሳፍንት 15:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍልስጥኤማውያንም፥ “ይህን ያደረገ ማን ነው?” አሉ። እነርሱም፥ “ሚስቱን ወስዶ ለሚዜው አጋብቶበታልና የቴምናታዊዉ አማች ሶምሶን ነው” አሉአቸው። ፍልስጥኤማውያንም ወጥተው የአባቷን ቤትና እርስዋን አባቷንም በእሳት አቃጠሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍልስጥኤማውያን፣ “ይህን ያደረገው ማን ነው?” ብለው ሲጠይቁ፣ “ሚስቱ ለሚዜው ስለ ተሰጠችበት የተምናዊው ዐማች ሳምሶን ነው” የሚል መልስ አገኙ። ስለዚህም ፍልስጥኤማውያን ወጥተው ሴቲቱንና አባቷን በእሳት አቃጥለው ገደሏቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍልስጥኤማውያን፥ “ይህን ያደረገው ማን ነው?” ብለው ሲጠይቁ፥ “ሚስተ ለሚዜው ስለ ተሰጠችበት የቲምናዊው ዐማች ሳምሶን ነው” የሚል መልስ አገኙ። ስለዚህም ፍልስጥኤማውያን ወጥተው ሴቲቱንና አባቷን በእሳት አቃጥለው ገደሏቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍልስጥኤማውያን ይህን ያደረገው ማን እንደሆን በጠየቁ ጊዜ፥ ሶምሶን መሆኑን ተረዱ፤ የቲምና ተወላጅ የሆነው ዐማቱ የሶምሶንን ሚስት ሚዜው ለነበረ ሌላ ሰው ሰጥቶበት ነበር፤ ስለዚህ ፍልስጥኤማውያን ሄደው ሴቲቱንና አባቷን በእሳት አቃጠሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍልስጥኤማውያንም፦ ይህን ያደረገው ማን ነው? አሉ። እነርሱም፦ ሚስቱን ወስዶ ለሚዜው አጋብቶበታልና የተምናዊው አማች ሶምሶን ነው አሉ። ፍልስጥኤማያንም ወጥተው ሴቲቱንና አባትዋን በእሳት አቃጠሉ። |
ሐሰትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል፥ የሥራውንም መቅሠፍት ይፈጽማል። እግዚአብሔር ደስ ብሎት የሚሰጥ ሰውን ይወድዳል፥ ከንቱ ሥራውን ግን ይጠላል።
አስቀድመን ደግሞ እንዳልናችሁና እንደ መሰከርንላችሁ፥ ጌታ ስለዚህ ነገር ሁሉ የሚበቀል ነውና፥ ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ፤ ወንድሙንም አያታልል።
የኤፍሬምም ሰዎች ተሰበሰቡ፤ ወደ ጻፎንም ተሻግረው ዮፍታሔን፥ “ከአሞን ልጆች ጋር ለመዋጋት ስታልፍ ከአንተ ጋር እንድንሄድ ስለምን አልጠራኸንም? ቤትህን በአንተ ላይ በእሳት እናቃጥለዋለን” አሉት።
ከዚህ በኋላ በአራተኛው ቀን የሶምሶንን ሚስት፥ “እንቆቅልሹን እንዲነግርሽ ባልሽን አባብይው፤ አለዚያም አንቺንና የአባትሽን ቤት በእሳት እናቃጥላለን፤ ወይስ ወደዚህ የጠራችሁን ልታደኸዩን ነውን?” አሉአት።
ችቦውንም አንድዶ በቆመው በፍልስጥኤማውያን እህል መካከል ሰደዳቸው፤ ነዶውንም፥ ክምሩንም፥ የቆመዉንም እህል፥ ወይኑንም፥ ወይራዉንም አቃጠለ።
ሶምሶንም አላቸው- “ይህን ብታደርጉም ደስ አይለኝም፤ በቀሌ ከአንድ ሰው ብቻ አይደለም፤ ሁላችሁንም እበቀላችኋለሁ፤ ከዚያም በኋላ አርፋለሁ።”