እርስዋም የመበለትነቷን ልብስ አወለቀች፤ መጐናጸፊያዋንም ለበሰች፤ ተሸፈነችም፤ ወደ ተምናም በሚወስደው መንገድ ዳር በኤናይም ደጅ ተቀመጠች፤ ሴሎም እንደ አደገ፥ ሚስትም ትሆነው ዘንድ እርስዋን ሊሰጠው እንዳልፈለገ አይታለችና።
መሳፍንት 15:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቷም፥ “ፈጽመህ ጠላህዋት ያልህ መስሎኝ ለሚዜህ አጋባኋት፤ ታናሽ እኅቷ ከእርስዋ ይልቅ የተዋበች አይደለችምን? እባክህ በእርስዋ ፋንታ አግባት” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባትየውም፣ “ፈጽሞ የጠላሃት መሆንህን ስለ ተረዳሁ ለሚዜህ ድሬለታለሁ፤ ታናሽ እኅቷ ከርሷ ይልቅ ውብ አይደለችምን? እርሷን አግባት” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባትየውም፥ “ፈጽሞ የጠላሃት መሆንህን ስለ ተረዳሁ ለሚዜህ ድሬለታለሁ፤ ታናሽ እኅቷ ከእርሷ ይልቅ ውብ አይደለችምን? እርሷን አግባት” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሶምሶንንም “አንተ የጠላሃት ስለ መሰለኝ ሚዜህ ለነበረው ሰው ዳርኳት፤ የሆነ ሆኖ የእርስዋ ታናሽ ይበልጥ ውብ አይደለችምን? እባክህ እርስዋን አግባት” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባትዋም፦ ፈጽመህ የጠላሃት መስሎኝ ለሚዜህ አጋባኋት፥ ታናሽ እኅትዋ ከርስዋ ይልቅ የተዋበች አይደለችምን? እባክህ፥ በእርስዋ ፋንታ አግባት አለው። |
እርስዋም የመበለትነቷን ልብስ አወለቀች፤ መጐናጸፊያዋንም ለበሰች፤ ተሸፈነችም፤ ወደ ተምናም በሚወስደው መንገድ ዳር በኤናይም ደጅ ተቀመጠች፤ ሴሎም እንደ አደገ፥ ሚስትም ትሆነው ዘንድ እርስዋን ሊሰጠው እንዳልፈለገ አይታለችና።
የሶምሶንም ሚስት በፊቱ እያለቀሰችበት፥ “ጠልተኸኛል፤ ከቶም አትወድደኝም፤ ለሕዝቤ ልጆች የነገርኸውን እንቆቅልሽህን አልነገርኸኝምና” አለችው። እርሱም፥ “እነሆ፥ ለአባቴና ለእናቴ አልነገርኋቸውም፤ ለአንቺ እነግርሻለሁን?” አላት።