Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 15:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 አባትየውም፥ “ፈጽሞ የጠላሃት መሆንህን ስለ ተረዳሁ ለሚዜህ ድሬለታለሁ፤ ታናሽ እኅቷ ከእርሷ ይልቅ ውብ አይደለችምን? እርሷን አግባት” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 አባትየውም፣ “ፈጽሞ የጠላሃት መሆንህን ስለ ተረዳሁ ለሚዜህ ድሬለታለሁ፤ ታናሽ እኅቷ ከርሷ ይልቅ ውብ አይደለችምን? እርሷን አግባት” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ሶምሶንንም “አንተ የጠላሃት ስለ መሰለኝ ሚዜህ ለነበረው ሰው ዳርኳት፤ የሆነ ሆኖ የእርስዋ ታናሽ ይበልጥ ውብ አይደለችምን? እባክህ እርስዋን አግባት” አለው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 አባ​ቷም፥ “ፈጽ​መህ ጠላ​ህ​ዋት ያልህ መስ​ሎኝ ለሚ​ዜህ አጋ​ባ​ኋት፤ ታናሽ እኅቷ ከእ​ር​ስዋ ይልቅ የተ​ዋ​በች አይ​ደ​ለ​ች​ምን? እባ​ክህ በእ​ር​ስዋ ፋንታ አግ​ባት” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 አባትዋም፦ ፈጽመህ የጠላሃት መስሎኝ ለሚዜህ አጋባኋት፥ ታናሽ እኅትዋ ከርስዋ ይልቅ የተዋበች አይደለችምን? እባክህ፥ በእርስዋ ፋንታ አግባት አለው።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 15:2
5 Referencias Cruzadas  

የመበለትነት ልብሷን አውልቃ፥ ማንነቷ እንዳይታወቅ ፊቷን በሻሽ ተከናንባ ወደ ተምና በሚወስደው መንገድ ዳር ባለች ኤናይም በተባለች ከተማ መግቢያ ላይ ተቀመጠች፤ ይህን ያደረገችው፥ ሴሎም ለአካለ መጠን ቢደርስም፥ እርሷን እንዲያገባ አባቱ አለመፈለጉን ስላወቀች ነው።


“እኔም ራሴ የናዝሬቱን የኢየሱስን ስም የሚቃወም እጅግ ነገር አደርግ ዘንድ እንዲገባኝ ይመስለኝ ነበር።


ከዚያ የሳምሶን ሚስት ተንሰቅስቃ እያለቀሰች ከፊቱ በመቅረብ፥ “ለካስ ትጠላኛለህ በእርግጥ አትወደኝም” አለችው። እርሱም፥ “ይህን ለአባቴም ሆነ ለእናቴ አልነገርኋቸውም፤ ታዲያ ለአንቺ ለምን እነግርሻለሁ?” አላት።


የሳምሶንም ሚስት ለሚዜው ተዳረች።


ሳምሶንም መልሶ፥ “ከእንግዲህ በፍልስጥኤማውያን ላይ በሚደርሰው ጉዳት ተጠያቂ አልሆንም” አላቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos