መሳፍንት 13:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም መልአክ፥ “ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠይቃለህ?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔርም መልአክ፣ “ስሜ ድንቅ ስለ ሆነ፣ ለምን ትጠይቀኛለህ?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታም መልአክ፥ “ስሜ ድንቅ ስለ ሆነ፥ ለምን ትጠይቀኛለህ?” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መልአኩም “ስሜን ለማወቅ የፈለግኸው ለምንድን ነው? ስሜ ድንቅ ነው” ሲል መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም መልአክ፦ ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠይቃለህ? አለው። |
በዚያም ስፍራ ባረከው። ያዕቆብም፥ “እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፤ ሰውነቴም ዳነች” ሲል የዚያን ቦታ ስም “ራእየ እግዚአብሔር” ብሎ ጠራው።
ሌዋውያኑም ኢያሱና ቀድምኤል፥ እንዲህ አሉ፥ “ቆማችሁ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም አምላካችንን እግዚአብሔርን አመስግኑ። የከበረ ስሙንም አመስግኑ፤ በበረከትና በምስጋናም ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አድርጉት።”
ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኀያል አምላክ፥ የዘለዓለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል፤
ሴቲቱም ወደ ባልዋ መጥታ፥ “አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ እኔ መጣ፤ መልኩም እንደ እግዚአብሔር መልአክ እጅግ የሚያስደነግጥ ነበረ፤ ከወዴትም እንደ መጣ ጠየቅሁት፥ እርሱም ስሙን አልነገረኝም።