ያዕቆብም እንዲህ ብሎ ስእለት ተሳለ፥ “እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ቢሆን፥ በምሄድባትም በዚች መንገድ ቢጠብቀኝ፥ የምበላውንም እንጀራ፥ የምለብሰውንም ልብስ ቢሰጠኝ፥
መሳፍንት 11:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮፍታሔም፥ “በእውነት የአሞንን ልጆች በእጄ አሳልፈህ ብትሰጠኝ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮፍታሔም እንዲህ ሲል ለእግዚአብሔር ተሳለ፤ “አሞናውያንን በእጄ አሳልፈህ ብትሰጠኝ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮፍታሔም እንዲህ ሲል ለጌታ ተሳለ፤ “አሞናውያንን በእጄ አሳልፈህ ብትሰጠኝ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ተሳለ፤ “በዐሞናውያን ላይ ድልን ብታቀዳጀኝ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮፍታሔም፦ በእውነት የአሞንን ልጆች በእጄ አሳልፈህ ብትሰጠኝ፥ |
ያዕቆብም እንዲህ ብሎ ስእለት ተሳለ፥ “እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ቢሆን፥ በምሄድባትም በዚች መንገድ ቢጠብቀኝ፥ የምበላውንም እንጀራ፥ የምለብሰውንም ልብስ ቢሰጠኝ፥
እስራኤልም ለእግዚአብሔር፥ “ይህን ሕዝብ አሳልፈህ በእጃችን ብትሰጠን እርሱንና ከተሞቹን ሕርም ብለን እናጠፋዋለን” ብለው ስእለት ተሳሉ።
የእግዚአብሔርም መንፈስ በዮፍታሔ ላይ መጣ፤ እርሱም የምናሴ ዕጣ ከምትሆን ከገለዓድ ምድርና ከገለዓድ መሴፋ፥ ወደ አሞን ልጆች ማዶ ተሻገረ።
ከአሞን ልጆች ዘንድ በደኅና በተመለስሁ ጊዜ፥ ከቤቴ ደጅ ወጥቶ የሚቀበለኝን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አደርገዋለሁ” ብሎ ለእግዚአብሔር ስእለት ተሳለ።
እርስዋም፥ “አዶናይ፥ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! የባርያህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝ፥ ለባርያህም ወንድ ልጅ ብትሰጥ ዕድሜውን ሁሉ ለአንተ እሰጠዋለሁ፤ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥም አይጠጣም። ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም” ብላ ስእለት ተሳለች።