ዘኍል 21:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 እስራኤልም ለእግዚአብሔር፥ “ይህን ሕዝብ አሳልፈህ በእጃችን ብትሰጠን እርሱንና ከተሞቹን ሕርም ብለን እናጠፋዋለን” ብለው ስእለት ተሳሉ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 በዚያ ጊዜ እስራኤል፣ “ይህን ሕዝብ አሳልፈህ በእጃችን ከሰጠኸን ከተሞቻቸውን ፈጽሞ እንደመስሳለን” ሲል ለእግዚአብሔር ተሳለ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 እስራኤልም ለጌታ እንዲህ ብሎ ስእለት ተሳለ፦ “እነዚህን ሕዝቦች ፈጽሞ አሳልፈህ በእጄ ብትሰጣቸው ከተሞቻቸውን እርም ብዬ አጠፋለሁ።” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 በዚያን ጊዜ እስራኤላውያን “ይህን ሕዝብ ድል እንድንነሣው ብትረዳን፥ እነርሱንም ሆኑ ከተሞቻቸውን ዳግመኛ እንዳያንሰራሩ አድርገን በፍጹም እንደመስሳቸዋለን” በማለት ለእግዚአብሔር ተሳሉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 እስራኤልም ለእግዚአብሔር፦ እነዚህን አሳልፈህ በእጄ ብትሰጣቸው ከተሞቻቸውን እርም ብዬ አጠፋለሁ ብሎ ስእለት ተሳለ። Ver Capítulo |