መሳፍንት 11:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮፍታሔም የላካቸው ወደ ዮፍታሔ ተመለሱ፤ ዮፍታሔም ወደ አሞን ልጆች ንጉሥ መልእክተኞችን እንደ ገና ላከ፤ እንዲህም አለው፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮፍታሔም መልእክተኞቹን እንደ ገና ወደ አሞናውያን ንጉሥ ላካቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮፍታሔም መልእክተኞቹን እንደገና ወደ አሞናውያን ንጉሥ ላካቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮፍታሔ እንደገና መልእክተኞችን ወደ ዐሞን ንጉሥ ላከ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮፍታሔም ወደ አሞን ልጆች ንጉሥ መልክተኞችን እንደ ገና ላከ፥ |
የአሞንም ልጆች ንጉሥ የዮፍታሔን መልእክተኞች፥ “እስራኤል ከግብፅ በወጣ ጊዜ ከአርኖን ጀምሮ እስከ ያቦቅና እስከ ዮርዳኖስ ድረስ ምድሬን ስለ ወሰደ ነው፤ አሁንም በሰላም መልሱልኝ” ብሎ መለሰላቸው።