በዚያችም ሌሊት ተነሣ፥ ሁለቱን ሚስቶቹንና ሁለቱን ዕቁባቶቹን ዐሥራ አንዱንም ልጆቹን ይዞ የያቦቅን ወንዝ ተሻገረ።
መሳፍንት 11:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአሞንም ልጆች ንጉሥ የዮፍታሔን መልእክተኞች፥ “እስራኤል ከግብፅ በወጣ ጊዜ ከአርኖን ጀምሮ እስከ ያቦቅና እስከ ዮርዳኖስ ድረስ ምድሬን ስለ ወሰደ ነው፤ አሁንም በሰላም መልሱልኝ” ብሎ መለሰላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአሞናውያንም ንጉሥ ለዮፍታሔ መልእክተኞች፣ “ይህን ያደረግሁት እስራኤል ከግብጽ በወጣ ጊዜ በአርኖንና በያቦቅ ወንዞች መካከል ያለውንና እስከ ዮርዳኖስ ያለውን አገሬን ስለ ወሰዱብኝ ነው፤ አሁንም በሰላም መልሱልኝ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአሞናውያንም ንጉሥ ለዮፍታሔ መልእክተኞች፥ “ይህን ያደረግሁት እስራኤል ከግብጽ በወጣ ጊዜ በአርኖንና በያቦቅ ወንዞች መካከል ያለውንና እስከ ዮርዳኖስ ያለውን አገሬን ስለ ወሰዱብኝ ነው፤ አሁንም በሰላም መልሱልኝ” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዐሞንም ንጉሥ ለዮፍታሔ መልእክተኞች መልስ ሲሰጥ “እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ ጊዜ ከአርኖን ወንዝ እስከ ያቦቅ ወንዝ ያለውን ምድሬንና የዮርዳኖስንም ወንዝ ወሰዱብኝ፤ አሁን ግን በሰላም መመለስ ይኖርባችኋል” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአሞንም ልጆች ንጉሥ የዮፍታሔን መልክተኞች፦ እስራኤል ከግብፅ በወጣ ጊዜ ከአርኖን ጀምሮ እስከ ያቦቅና እስከ ዮርዳኖስ ድረስ ምድሬን ስለ ወሰደ ነው፥ አሁንም በሰላም መልሱልኝ ብሎ መለሰላቸው። |
በዚያችም ሌሊት ተነሣ፥ ሁለቱን ሚስቶቹንና ሁለቱን ዕቁባቶቹን ዐሥራ አንዱንም ልጆቹን ይዞ የያቦቅን ወንዝ ተሻገረ።
ዳሩ ግን አምላካችን እግዚአብሔር እንዳዘዘን ወደ አሞን ልጆች ምድር፥ በያቦቅም ወንዝ አጠገብ ወደ አለው ስፍራ ሁሉ፥ በተራራማውም ሀገር ወደ አሉ ከተሞች አልደረስንም።
ለሮቤልና ለጋድም ከገለዓድ ምድር ጀምሮ እስከ አርኖን ሸለቆ ድረስ የሸለቆውን እኩሌታ ዳርቻውንም፥ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ እስከ ኢያቦቅ ወንዝ ድረስ፥
ዮፍታሔም ወደ አሞን ልጆች ንጉሥ፥ “ሀገሬን ለመውጋት ወደ እኔ የምትመጣ አንተ ከእኔ ጋር ምን አለህ?” ብሎ መልእክተኞችን ላከ።
ዮፍታሔም የላካቸው ወደ ዮፍታሔ ተመለሱ፤ ዮፍታሔም ወደ አሞን ልጆች ንጉሥ መልእክተኞችን እንደ ገና ላከ፤ እንዲህም አለው፦