La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መሳፍንት 1:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ይሁ​ዳም ወን​ድ​ሙን ስም​ዖ​ንን፥ “ከእኔ ጋር ወደ ዕጣዬ ውጣ፤ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንም እን​ው​ጋ​ቸው፤ እኔም ደግሞ ከአ​ንተ ጋር ወደ ዕጣህ እሄ​ዳ​ለሁ” አለው። ስም​ዖ​ንም ከእ​ርሱ ጋር ሄደ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የይሁዳም ሰዎች ወንድሞቻቸውን የስምዖንን ልጆች፣ “ከነዓናውያንን ለመውጋት ድርሻችን ወደ ሆነው ምድር ዐብረን እንውጣ፤ እኛም እንደዚሁ ድርሻችሁ ወደ ሆነው ምድር ዐብረናችሁ እንወጣለን” አሏቸው፤ ስለዚህም የስምዖን ሰዎች ዐብረዋቸው ሄዱ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ይሁዳም ወንድሙን ስምዖንን፦ “ከነዓናውያንን ለመውጋት ድርሻዬ ወደ ሆነው ምድር አብረን እንውጣ፤ እኔም እንደዚሁ ድርሻህ ወደ ሆነው ምድር አብሬህ እወጣለሁ” አለው። ስለዚህም ከእርሱ ጋር ሄደ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የይሁዳ ነገድ ሕዝቦች ወንድሞቻቸውን የስምዖንን ነገድ ሕዝቦች “ለእኛ ወደ ተደለደለው ርስት በከነዓናውያን ላይ ለመዝመት ከእኛ ጋር አብረን እንሂድ እኛም ለእናንተ ወደተደለደለው ርስት አብረን እንሄዳለን” አሉአቸው። የስምዖን ነገድ ሕዝቦች ከእነርሱ ጋር ሄዱ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ይሁዳም ወንድሙን ስምዖንን፦ ከነዓናውያንን እንወጋ ዘንድ ከእኔ ጋር ወደ ዕጣዬ ውጣ፥ እኔም ደግሞ ከአንተ ጋር ወደ ዕጣህ እሄዳለሁ አለው። ስምዖንም ከእርሱ ጋር ሄደ።

Ver Capítulo



መሳፍንት 1:3
7 Referencias Cruzadas  

ልያም ዳግ​መኛ ፀነ​ሰች፤ ሁለ​ተኛ ወንድ ልጅ​ንም ለያ​ዕ​ቆብ ወለ​ደ​ች​ለት፤ “እኔ እንደ ተጠ​ላሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ሰማ ይህን ጨመ​ረ​ልኝ” አለች፤ ስሙ​ንም ስም​ዖን ብላ ጠራ​ችው ።


እር​ሱም አለው፥ “ሶር​ያ​ው​ያን ቢበ​ረ​ቱ​ብኝ ትረ​ዳ​ኛ​ለህ፤ የአ​ሞን ልጆ​ችም ቢበ​ረ​ቱ​ብህ እኔ መጥቼ እረ​ዳ​ሃ​ለሁ።


ሁለ​ተ​ኛ​ውም ዕጣ ለስ​ም​ዖን ልጆች ነገድ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ወጣ፤ ርስ​ታ​ቸ​ውም በይ​ሁዳ ልጆች ርስት መካ​ከል ነበረ።


ከስምዖን ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከሌዊ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከይሳኮር ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥


ይሁ​ዳም ከወ​ን​ድሙ ከስ​ም​ዖን ጋር ሄደ፤ በሴ​ፌት የተ​ቀ​መ​ጡ​ት​ንም ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን መቱ፤ ፈጽ​መ​ውም አጠ​ፉ​አት፤ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ስም ሕርም ብለው ጠሩ​አት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ይሁዳ ይውጣ፤ እነሆ፥ ምድ​ሪ​ቱን በእጁ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቼ​አ​ታ​ለሁ” አለ።


ይሁ​ዳም ወጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንና ፌር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን በእጁ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም በቤ​ዜቅ ውስጥ ዐሥር ሺህ ሰዎ​ችን ገደ​ለ​ባ​ቸው።