ነገር ግን ቀስቶቻቸው በኀይል ተቀጠቀጡ፤ የእጆቻቸው ክንድ ሥርም በያዕቆብ ኀያል እጅ ዛለ፤ በዚያም በአባትህ አምላክ ዘንድ እስራኤልን አጸናው።
መሳፍንት 1:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዮሴፍም ልጆች ደግሞ ወደ ቤቴል ወጡ፤ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዮሴፍ ወገን ደግሞ ቤቴልን ወጉ፤ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋራ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዮሴፍ ወገን ደግሞ ቤቴልን ሊወጉ ወጡ፤ ጌታም ከእነርሱ ጋር ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዮሴፍ ዘሮች ደግሞ በቤቴል ላይ ዘመቱ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዮሴፍም ወገን ደግሞ በቤቴል ላይ ወጡ፥ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ነበረ። |
ነገር ግን ቀስቶቻቸው በኀይል ተቀጠቀጡ፤ የእጆቻቸው ክንድ ሥርም በያዕቆብ ኀያል እጅ ዛለ፤ በዚያም በአባትህ አምላክ ዘንድ እስራኤልን አጸናው።
በምናሴም ልጆች ዳርቻ ቤትሳንና መንደሮችዋ፥ ታዕናክና መንደሮችዋ፥ መጊዶና መንደሮችዋ፥ ዶርና መንደሮችዋ፥ በላድና መንደሮችዋ ነበሩ፤ በእነዚህ ያዕቆብ የተባለ የእስራኤል ልጅ የዮሴፍ ልጆች ተቀመጡ።
የምናሴ ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች- እንደ እየስማቸው ቍጥር፥ በየራሳቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚወጡት ሁሉ፥
የዮሴፍ ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ሁለት ነገዶች ነበሩ፤ ለሌዋውያንም ከሚቀመጡባቸው ከተሞች ለእንስሶቻቸው ከሚሆን ማሰማሪያቸውና ከእንስሶቻቸውም በቀር በምድሩ ውስጥ ድርሻ አልሰጡአቸውም።
እግዚአብሔርም ከይሁዳ ጋር ነበረ፤ ይሁዳም ተራራማውን ሀገር ወረሰ፤ በሸለቆው የሚኖሩትን ግን የብረት ሰረገሎች ነበሩአቸውና ሊወርሳቸው አልቻለም።
ነገር ግን በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሴዎናውያንን የብንያም ልጆች አላወጡአቸውም፤ ኢያቡሴዎናውያንም ከብንያም ልጆች ጋር እስከ ዛሬ ድረስ በኢየሩሳሌም ተቀምጠዋል።