La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 8:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በያ​ዛ​ች​ኋ​ትም ጊዜ ከተ​ማ​ዪ​ቱን በእ​ሳት አቃ​ጥ​ሉ​አት፤ እንደ አል​ኋ​ችሁ አድ​ርጉ፤ እነሆ፥ አዝ​ዣ​ች​ኋ​ለሁ።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከተማዪቱን ስትይዙም በእሳት አቃጥሏት፤ እግዚአብሔር ያዘዘውንም አድርጉ፤ እነሆ አዝዣችኋለሁ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በያዛችኋትም ጊዜ ከተማይቱን በእሳት አቃጥሉአት፤ እንደ ጌታ ቃል አድርጉ፤ እነሆ፥ አዝዣችኋለሁ።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከተማይቱን ከያዛችሁ በኋላ፥ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት በእሳት አቃጥሉአት። እነሆ፥ አዝዤአችኋለሁ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በያዛችኋትም ጊዜ ከተማይቱን በእሳት አቃጥሉአት፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል አድርጉ፥ እነሆ፥ አዝዣችኋለሁ።

Ver Capítulo



ኢያሱ 8:8
12 Referencias Cruzadas  

አቤ​ሴ​ሎ​ምም እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ አደ​ረገ፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን፥ “አም​ኖን የወ​ይን ጠጅ ጠጥቶ ልቡን ደስ ባለው ጊዜ እዩ፦ አም​ኖ​ንን ግደሉ ባል​ኋ​ችሁ ጊዜ ግደ​ሉት። አት​ፍ​ሩም፤ ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁም እኔ ነኝና በርቱ፤ ጽኑም” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው።


ከእ​ነ​ር​ሱም ምንም ነፍስ አታ​ድ​ንም።


እነ​ር​ሱም ለኢ​ያሱ እን​ዲህ ብለው መለ​ሱ​ለት፥ “ያዘ​ዝ​ኸ​ንን ነገር ሁሉ እና​ደ​ር​ጋ​ለን ወደ​ም​ት​ል​ከ​ንም ስፍራ እን​ሄ​ዳ​ለን።


እነሆ አዝ​ዝ​ሃ​ለሁ፤ በም​ት​ሄ​ድ​በት ሁሉ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና ጽና፥ በርታ፤ አት​ፍራ፥ አት​ደ​ን​ግ​ጥም።”


ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም፥ በእ​ር​ስ​ዋም የነ​በ​ረ​ውን ሁሉ በእ​ሳት አቃ​ጠሉ፤ ነገር ግን ብሩ​ንና ወር​ቁን፥ የና​ሱ​ንና የብ​ረ​ቱ​ንም ዕቃ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግምጃ ቤት ውስጥ አገቡ።


ሕዝ​ቡም ሁሉ ሠራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን በከ​ተ​ማው መስዕ በኩል አኖሩ፤ ዳር​ቻ​ውም እስከ ከተ​ማው ባሕር ድረስ ነው፤ ኢያ​ሱም በዚ​ያች ሌሊት ወደ ሸለ​ቆው መካ​ከል ሄደ።


በኢ​ያ​ሪ​ኮና በን​ጉ​ሥ​ዋም እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ እን​ዲሁ በጋ​ይና በን​ጉ​ሥዋ ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ የከ​ብ​ቱን ምርኮ ግን ለራ​ሳ​ችሁ ትዘ​ር​ፋ​ላ​ችሁ፤ ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም በስ​ተ​ኋላ ይከ​ብ​ቧት ዘንድ ጦር ላክ” አለው።


እነ​ዚ​ያም ከከ​ተማ ወጥ​ተው ተቀ​በ​ሉ​አ​ቸው፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሠራ​ዊት መካ​ከ​ልም አገ​ቡ​አ​ቸው፤ እኒያ ከወ​ዲያ፥ እኒ​ህም ከወ​ዲህ ሆነው አንድ እን​ኳን ሳይ​ቀ​ርና ሳያ​መ​ልጥ ገደ​ሉ​አ​ቸው።


ኢያ​ሱም ከተ​ማ​ዋን በእ​ሳት አቃ​ጠ​ላት፤ ዐመ​ድም ሆነች፤ እስከ ዛሬም ድረስ ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ የሚ​ኖ​ር​ባት እን​ዳ​ይ​ኖር አደ​ረ​ጋት።


እን​ግ​ዲህ እና​ን​ተም ከተ​ደ​በ​ቃ​ች​ሁ​በት ስፍራ ተነሡ፤ አም​ላ​ካ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እር​ስ​ዋን በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ልና ከተ​ማ​ዪ​ቱን ያዙ።


ኢያ​ሱም ላካ​ቸው፤ ወደ​ሚ​ደ​በ​ቁ​በ​ትም ስፍራ ሄዱ፤ በጋ​ይና በቤ​ቴል መካ​ከ​ልም በጋይ በባ​ሕር በኩል ተቀ​መጡ፤ ኢያሱ ግን በዚ​ያች ሌሊት በሕ​ዝቡ መካ​ከል አደረ።


ዲቦ​ራም ልካ ከቃ​ዴስ ንፍ​ታ​ሌም የአ​ቢኒ​ሔ​ምን ልጅ ባር​ቅን ጠርታ እን​ዲህ አለ​ችው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ ያዘ​ዘህ አይ​ደ​ለ​ምን? ሄደህ ወደ ታቦር ተራራ ውጣ፤ ከአ​ን​ተም ጋር ከን​ፍ​ታ​ሌ​ምና ከዛ​ብ​ሎን ልጆች ዐሥር ሺህ ሰዎች ውሰድ፤