La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 8:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወጥ​ተ​ውም በተ​ከ​ተ​ሉን ጊዜ ከከ​ተማ እና​ር​ቃ​ቸ​ዋ​ለን፤ እነ​ር​ሱም እንደ በፊቱ ከፊ​ታ​ችን ሸሹ ይላሉ፤ እኛም ከፊ​ታ​ቸው እን​ሸ​ሻ​ለን።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነርሱም፣ ‘ከዚህ ቀደም እንዳደረጉት አሁንም ከእኛ በመሸሽ ላይ ናቸው’ በማለት ከከተማዪቱ እስክናርቃቸው ድረስ ይከታተሉናል፤ በዚህ ሁኔታ እኛም እንሸሻለን፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነርሱም፦ ‘እንደ ቀድሞው ከእኛ ዘንድ እየሸሹ ናቸው’ ይላሉና ከከተማይቱ እስክናርቃቸው ድረስ ወጥተው ይከተሉናል፤ እኛም ከፊታቸው እንሸሻለን።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከእነርሱ እየሸሸን ሳለን እንደ ቀድሞው ከእኛ እየሸሹ ነው ይላሉ፤ ከከተማው እስክናርቃቸው ድረስ እኛን ይከተላሉ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አስቀድመን እንደ ሸሸን የምንሸሽ ይመስላቸዋልና ከከተማይቱ እስክናርቃቸው ድረስ ወጥተው ይከተሉናል፥ እኛም ከፊታቸው እንሸሻለን።

Ver Capítulo



ኢያሱ 8:6
7 Referencias Cruzadas  

ፈር​ዖ​ንም ለሕ​ዝቡ ስለ እስ​ራ​ኤል ልጆች፦ ‘በም​ድር ይቅ​በ​ዘ​በ​ዛሉ፤ ምድረ በዳም ዘጋ​ቻ​ቸው’ ይላል።


ጠላ​ትም፦ ‘አሳ​ድጄ እይ​ዛ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ምር​ኮም እካ​ፈ​ላ​ለሁ፤ ነፍ​ሴ​ንም አጠ​ግ​ባ​ታ​ለሁ፤ በሰ​ይ​ፌም እገ​ድ​ላ​ለሁ፤ በእ​ጄም እገ​ዛ​ለሁ’ አለ።


ክፉን ከሚ​ያ​ደ​ርጉ ወገን ፈጥኖ ክር​ክ​ርን የሚ​ያ​ደ​ርግ የለ​ምና፤ ስለ​ዚህ የሰው ልጆች ልብ በእ​ነ​ርሱ ክፉን ለመ​ሥ​ራት ጠነ​ከረ።


ሰውም ጊዜ​ውን አያ​ው​ቅም፤ በክፉ መረብ እንደ ተጠ​መዱ ዓሣ​ዎች ፥ በወ​ጥ​መ​ድም እንደ ተያዙ ወፎች፥ እን​ዲሁ የሰው ልጆች በክፉ ጊዜ በድ​ን​ገት ሲወ​ድ​ቅ​ባ​ቸው ይጠ​መ​ዳሉ።


እኔ፥ ከእ​ኔም ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ ወደ ከተ​ማ​ዪቱ እን​ቀ​ር​ባ​ለን፤ የጋ​ይም ሰዎች እኛን ሊገ​ናኙ እንደ ፊተ​ኛው በወጡ ጊዜ ከፊ​ታ​ቸው እን​ሸ​ሻ​ለን፤


እን​ግ​ዲህ እና​ን​ተም ከተ​ደ​በ​ቃ​ች​ሁ​በት ስፍራ ተነሡ፤ አም​ላ​ካ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እር​ስ​ዋን በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ልና ከተ​ማ​ዪ​ቱን ያዙ።


የብ​ን​ያ​ምም ልጆች፥ “እንደ ቀድ​ሞው በፊ​ታ​ችን ይሞ​ታሉ” አሉ። የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ግን፥ “እን​ሽሽ፤ ከከ​ተ​ማም ወደ መን​ገድ እና​ር​ቃ​ቸው” አሉ።