La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 8:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኢያ​ሱም ማልዶ ተነሣ፤ ሕዝ​ቡ​ንም አያ​ቸው፤ እር​ሱም፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ከሕ​ዝቡ በፊት ወደ ጋይ ወጡ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በማግስቱም ጧት ኢያሱ ማልዶ በመነሣት ወንዶቹን ሰበሰበ፤ እርሱና የእስራኤል አለቆችም ከፊት ሆነው እየመሯቸው ወደ ጋይ ወጡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢያሱም ማልዶ በጠዋት ተነሣ፥ ሕዝቡንም ሰበሰበ፤ እርሱም ከእስራኤል ሽማግሌዎች ጋር ከሕዝቡ በፊት ወደ ጋይ ወጡ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በማግስቱም ጠዋት ኢያሱ ቀደም ብሎ በመነሣት ሕዝቡን ጠራ፤ እርሱና የእስራኤል መሪዎች ሁሉ ዘማቹን ጦር ወደ ዐይ መምራት ጀመሩ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢያሱም ማልዶ ተነሣ፥ ሕዝቡንም አሰለፈ፥ እርሱም የእስራኤልም ሽማግሌዎች ከሕዝቡ በፊት ወደ ጋይ ወጡ።

Ver Capítulo



ኢያሱ 8:10
7 Referencias Cruzadas  

አብ​ር​ሃ​ምም በማ​ለዳ ተነ​ሥቶ አህ​ያ​ውን ጫነ፤ ሁለ​ቱ​ንም ሎሌ​ዎ​ቹ​ንና ልጁን ይስ​ሐ​ቅን ከእ​ርሱ ጋር ወሰደ፤ ዕን​ጨ​ት​ንም ለመ​ሥ​ዋ​ዕት ሰነ​ጠቀ፤ ተነ​ሥ​ቶም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዳ​ለው ቦታ ሄደ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ደረሰ።


ኢያ​ሱም ማልዶ ተነሣ፤ እር​ሱና እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ከሰ​ጢም ተጕ​ዘው ወደ ዮር​ዳ​ኖስ መጡ፤ ሳይ​ሻ​ገ​ሩም በዚያ አደሩ።


ኢያ​ሱም በማ​ግ​ሥቱ ማለዳ ተነሣ፤ ካህ​ና​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሕ​ጉን ታቦት ተሸ​ከሙ።


ኢያ​ሱም ማልዶ ተነሣ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም በየ​ነ​ገ​ዶ​ቻ​ቸው ሰበ​ሰ​ባ​ቸው፤ በይ​ሁ​ዳም ነገድ ላይ ምል​ክት ታየ፤


ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ ተዋ​ጊ​ዎች ሕዝብ ሁሉ ወጥ​ተው ቀረቡ፤ ወደ ከተ​ማ​ዪ​ቱም ፊት ደረሱ፤ በጋ​ይም በም​ሥ​ራቅ በኩል ሰፈሩ፤ በእ​ነ​ር​ሱና በጋ​ይም መካ​ከል ሸለቆ ነበረ።


ኢያ​ሱም ላካ​ቸው፤ ወደ​ሚ​ደ​በ​ቁ​በ​ትም ስፍራ ሄዱ፤ በጋ​ይና በቤ​ቴል መካ​ከ​ልም በጋይ በባ​ሕር በኩል ተቀ​መጡ፤ ኢያሱ ግን በዚ​ያች ሌሊት በሕ​ዝቡ መካ​ከል አደረ።