Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢያሱ 8:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ኢያሱም ማልዶ በጠዋት ተነሣ፥ ሕዝቡንም ሰበሰበ፤ እርሱም ከእስራኤል ሽማግሌዎች ጋር ከሕዝቡ በፊት ወደ ጋይ ወጡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በማግስቱም ጧት ኢያሱ ማልዶ በመነሣት ወንዶቹን ሰበሰበ፤ እርሱና የእስራኤል አለቆችም ከፊት ሆነው እየመሯቸው ወደ ጋይ ወጡ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 በማግስቱም ጠዋት ኢያሱ ቀደም ብሎ በመነሣት ሕዝቡን ጠራ፤ እርሱና የእስራኤል መሪዎች ሁሉ ዘማቹን ጦር ወደ ዐይ መምራት ጀመሩ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ኢያ​ሱም ማልዶ ተነሣ፤ ሕዝ​ቡ​ንም አያ​ቸው፤ እር​ሱም፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ከሕ​ዝቡ በፊት ወደ ጋይ ወጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ኢያሱም ማልዶ ተነሣ፥ ሕዝቡንም አሰለፈ፥ እርሱም የእስራኤልም ሽማግሌዎች ከሕዝቡ በፊት ወደ ጋይ ወጡ።

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 8:10
7 Referencias Cruzadas  

በማግስቱም ጠዋት አብርሃም በማለዳ ተነሥቶ ለመሥዋዕት የሚሆን ዕንጨትን ቈረጠና በአህያው ላይ ጫነው፥ ከእርሱም ጋር ሁለቱን አገልጋዮቹን እና ልጁን ይስሕቅን ይዞ፥ እግዚአብሔር ወዳለው ቦታ ተነሥቶ ጉዞ ጀመረ።


ትእዛዝህን ለመጠበቅ ጨከንሁ አልዘገየሁምም።


በማግስቱም ኢያሱ ማልዶ ተነሣ፥ እርሱና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ከሰጢም ተነሥተው ወደ ዮርዳኖስ መጡ፤ ሳይሻገሩም በዚያ አደሩ።


ከዚያም በኋላ ኢያሱ ማልዶ ተነሣ፤ ካህናቱም የጌታን ታቦት ተሸከሙ።


ኢያሱም ማልዶ ተነሣ፥ እስራኤልንም በየነገዶቻቸው አቀረበ፤ የይሁዳም ነገድ ተለየ፤


ከእርሱም ጋር የነበሩ ተዋጊዎች ሁሉ ወጥተው በመጓዝ ወደ ከተማይቱ ቀረቡ፥ በጋይም በሰሜን በኩል ሰፈሩ፤ በእነርሱና በጋይም መካከል ሸለቆ ነበረ።


ኢያሱም ሰደዳቸው፤ ወደሚደበቁበትም ስፍራ ሄዱ፥ በጋይና በቤቴል መካከልም በጋይ በምዕራብ በኩል ተቀመጡ፤ ኢያሱ ግን በዚያች ሌሊት በሕዝቡ መካከል አደረ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos