የከለዳውያንም ሠራዊት ንጉሡን ተከተሉ፤ በኢያሪኮም በኩል ባለው ሜዳ ያዙት፤ ሠራዊቱም ሁሉ ከእርሱ ተለይተው ተበትነው ነበር።
ኢያሱ 4:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አርባ ሺህ ያህል ለጦርነት የታጠቁ ሰዎች የኢያሪኮን ሀገር ይወጉ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ተሻገሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አርባ ሺሕ ያህሉ ጦርና ጋሻቸውን ይዘው፣ ለውጊያ ዝግጁ ሆነው፣ በእግዚአብሔር ፊት ወደ ኢያሪኮ ሜዳ ተሻገሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አርባ ሺህ ያህል ሰዎች መሣርያ ታጥቀው ለጦርነት በጌታ ፊት ወደ ኢያሪኮ ሜዳ ተሻገሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእነርሱም የተውጣጡ ብዛታቸው አርባ ሺህ ያኽል የሆነ ጦረኞች በእግዚአብሔር ፊት ተሰልፈው በኢያሪኮ አቅራቢያ ወደሚገኘው ሜዳ ተሻገሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አርባ ሺህ ያህል ሰዎች ጋሻና ጦራቸውን ይዘው ለሰልፍ በእግዚአብሔር ፊት ወደ ኢያሪኮ ሜዳ ተሻገሩ። |
የከለዳውያንም ሠራዊት ንጉሡን ተከተሉ፤ በኢያሪኮም በኩል ባለው ሜዳ ያዙት፤ ሠራዊቱም ሁሉ ከእርሱ ተለይተው ተበትነው ነበር።
ነገር ግን እግዚአብሔር ሕዝቡን በዙሪያ መንገድ በኤርትራ ባሕር ባለችው ምድረ በዳ መራቸው። የእስራኤልም ልጆች በአምስተኛው ትውልድ ከግብፅ ምድር ወጡ።
የከለዳውያንም ሠራዊት ተከታተላቸው፤ ሴዴቅያስንም በኢያሪኮ ሜዳ አገኙት፤ ይዘውም በሐማት ምድር ወዳለችው ወደ ዴብላታ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነፆር አመጡት፤ እርሱም ፍርድን በእርሱ ላይ ተናገረ።
የከለዳውያንም ሠራዊት ንጉሡን ተከታተሉት፤ በኢያሪኮም ሜዳ ሴዴቅያስን ያዙ፤ ሠራዊቱም ሁሉ ከእርሱ ዘንድ ተበትነው ነበር።
እኛ ግን ለጦርነት ታጥቀን ወደ ስፍራቸው እስክናገባቸው ድረስ በእስራኤል ልጆች ፊት እንሄዳለን፤ በዚህም ምድር ስላሉ ሰዎች ልጆቻችን በተመሸጉ ከተሞች ይቀመጣሉ።
“በዚያም ዘመን እንዲህ ብዬ አዘዝኋችሁ፦ አምላካችሁ እግዚአብሔር ይህችን ምድር ርስት አድርጎ ሰጥቶአችኋል፤ መሣሪያችሁን ይዛችሁ እናንተ አርበኞች ሁሉ በወንድሞቻችሁ በእስራኤል ልጆች ፊት ትሻገራላችሁ።
በዚያም ቀን እግዚአብሔር ኢያሱን በእስራኤል ልጆች ሁሉ ፊት ከፍ አደረገው፤ ሙሴንም እንደ ፈሩ በዕድሜው ሁሉ ፈሩት።
የእስራኤልም ልጆች በጌልገላ ሰፈሩ፤ ከወሩም በዐሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በዮርዳኖስ ማዶ በኢያሪኮ ምዕራብ ፋሲካን አደረጉ።
የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ወጡ፤ ማኅበሩም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ፥ ከገለዓድም ሰዎች ጋር፥ ወደ እግዚአብሔር ወደ መሴፋ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰበሰቡ።