እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፥ “ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ” አለው። አብራምም ለእርሱ ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ መሠውያን ሠራ።
ኢያሱ 22:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በከነዓን ምድር ወዳለው ወደ ዮርዳኖስ አቅራቢያም ወደ ገለዓድ በመጡ ጊዜ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ በዚያ በዮርዳኖስ አጠገብ የሚታይ ታላቅ መሠዊያ ሠሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሮቤልና የጋድ እንዲሁም የምናሴ ነገድ እኩሌታ በከነዓን ምድር ወዳለችው፣ ዮርዳኖስ አጠገብ ወደምትገኘው ገሊሎት ወደ ተባለች ስፍራ ሲደርሱ በወንዙ አጠገብ ግዙፍ መሠዊያ ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በከነዓን ምድር ወዳለው ወደ ዮርዳኖስ አቅራቢያም በመጡ ጊዜ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ በዚያ በዮርዳኖስ አጠገብ ታላቅ መሠዊያ ሠሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሮቤል፥ የጋድና የምሥራቅ ምናሴ ነገዶች በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ በከነዓን ምድር ወደሚገኘው ወደ ገሊሎት እንደ ደረሱ በወንዙ አጠገብ አስደናቂ የሆነ ታላቅ መሠዊያ ሠሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በከነዓን ምድር ወዳለው ወደ ዮርዳኖስ አቅራቢያም በመጡ ጊዜ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ በዚያ በዮርዳኖስ አጠገብ ታላቅ መሠዊያ ሠሩ። |
እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፥ “ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ” አለው። አብራምም ለእርሱ ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ መሠውያን ሠራ።
ከዚያም በቤቴል ምሥራቅ ወዳለው ተራራ ወጣ፤ በዚያም ቤቴልን ወደ ምዕራብ፥ ጋይን ወደ ምሥራቅ አድርጎ ድንኳኑን ተከለ፤ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠውያን ሠራ፤ የእግዚአብሔርንም ስም ጠራ።
ያዕቆብም ማልዶ ተነሣ፤ ተንተርሷት የነበረችውንም ድንጋይ ወስዶ ሐውልት አድርጎ አቆማት፥ በላይዋም ዘይትን አፈሰሰባት።
በዚያ ቀን በግብፅ ምድር መካከል አንዲቱ ከተማ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ትሆናለች፤ በዳርቻዋም ለእግዚአብሔርዐምድ ይሆናል።
የእስራኤልም ልጆች በከነዓን ምድር ዳርቻ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው በገለዓድ፥ የእስራኤል ልጆች ባሉበት ወገን፥ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ መሠዊያ እንደ ሠሩ ሰሙ።
የሮቤልም ልጆች የጋድም ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ ሄዱ፤ በሙሴም እጅ በተሰጠ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ተቀበሉት ወደ ርስታቸው ወደ ገለዓድ ምድር ይገቡ ዘንድ በከነዓን ምድር ካለችው ከሴሎ ከእስራኤል ልጆች ዘንድ ተመለሱ።