ኢያሱ 21:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሌዊ ወገኖች የቀሩት የሜራሪ ልጆች ከተሞች ሁሉ በየወገኖቻቸው እነዚህ ነበሩ፤ ዕጣቸውም ዐሥራ ሁለት ከተማ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሜራሪ ጐሣዎች ለሆኑት ለተቀሩት ሌዋውያን የተመደቡት ከተሞች ሁሉ ዐሥራ ሁለት ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሌዋውያን ወገኖች የቀሩት የሜራሪ ልጆች ከተሞች ሁሉ በየወገኖቻቸው እነዚህ ነበሩ፤ ዕጣቸውም ዐሥራ ሁለት ከተማ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሌዋውያን ነገድ ለሆኑት ለቀሪዎቹ የሜራሪ ጐሣዎች የተሰጡት ዐሥራ ሁለት ከተሞች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሌዋውያን ወገኖች የቀሩት የሜራሪ ልጆች ከተሞች ሁሉ በየወገኖቻቸው እነዚህ ነበሩ፥ ዕጣቸውም አሥራ ሁለት ከተማ ነበረ። |
በእስራኤል ልጆች ርስት መካከል የነበሩት የሌዋውያን ከተሞች ሁሉ በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ ካሉ ከመሰማርያዎቻቸው ጋር አርባ ስምንት ከተሞች ነበሩ።