ከኬብሮናውያንም እንደ አባቶች ቤቶች ትውልዶች የኬብሮናውያን አለቃ ኤርያስ ነበረ። ዳዊት በነገሠ በአርባኛው ዓመት ይፈልጉአቸው ነበረ፤ በእነርሱም መካከል በገለዓድ ኢያዜር ጽኑዓን ኀያላን ሰዎች ተገኙ፤
ኢያሱ 21:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐሴቦንንና መሰማርያዋን፥ ኢያዜርንና መሰማርያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐሴቦንና ኢያዜር፣ እነዚህ አራት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሐሴቦንንና መሰማሪያዋን፥ ኢያዜርንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሐሴቦንና ያዕዜር ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሐሴቦንንና መሰምርያዋን፥ ኢያዜርንና መሰምርያዋን፥ አራቱን ከተሞች ሰጡ። |
ከኬብሮናውያንም እንደ አባቶች ቤቶች ትውልዶች የኬብሮናውያን አለቃ ኤርያስ ነበረ። ዳዊት በነገሠ በአርባኛው ዓመት ይፈልጉአቸው ነበረ፤ በእነርሱም መካከል በገለዓድ ኢያዜር ጽኑዓን ኀያላን ሰዎች ተገኙ፤
አንቺ የሴባማ ወይን ሆይ! የኢያዜርን ልቅሶ ለአንቺ አለቅሳለሁ፤ ቅርንጫፎችሽ ባሕርን ተሻግረዋል፤ ወደ ኢያዜርም ባሕር ደርሰዋል፤ ሳይበስል በሰብልሽና በወይንሽ ላይ ጥፋት መጥቶአል።
ለሮቤል ልጆችና ለጋድ ልጆች እጅግ ብዙ እንስሶች ነበሩአቸው፤ እነሆም፥ የኢያዜር ምድርና የገለዓድ ምድር የከብት ሀገር እንደ ነበረ አዩ።
የሚሶር ከተሞች ሁሉ፥ በሐሴቦንም የነገሠው የአሞሬዎናውያን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ሁሉ ነበረ፤ ሙሴም እርሱንና በምድሪቱ የተቀመጡትን የሴዎንን መሳፍንት፥ የምድያምን አለቆች ኤዊን፥ ሮቦቅን፥ ሱርን፥ ኡርን፥ ሮቤን በሲዮን የሚኖሩትንም ገደላቸው።
ድንበራቸውም ኢያዜርና የገለዓድ ከተሞች ሁሉ፥ የአሞንም ልጆች ምድር እኩሌታ በራባት ፊት እስካለችው እስከ አሮዔር ድረስ፥
ከጋድም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገለዓድ ውስጥ ራሞትንና መሰማርያዋን፥ ቃሚንንና መሰማርያዋን፤