“ከቄድሞትም ምድረ በዳ የሰላምን ቃል ይነግሩት ዘንድ ወደ ሐሴቦን ንጉሥ ወደ ሴዎን እንዲህ ብዬ መልእክተኞችን ላክሁ፦
ኢያሱ 21:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቄዴሞትንና መሰማርያዋን፥ ሜፍዐትንና መሰማርያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቅዴሞትና ሜፍዓት፣ እነዚህ አራት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቅዴሞትንና መሰማሪያዋን፥ ሜፍዓትንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀዴሞትና ሜፋዓት ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቅዴሞትንና መሰምርያዋን፥ ሜፍዓትንና መሰምርያዋን፥ አራቱን ከተሞች ሰጡ። |
“ከቄድሞትም ምድረ በዳ የሰላምን ቃል ይነግሩት ዘንድ ወደ ሐሴቦን ንጉሥ ወደ ሴዎን እንዲህ ብዬ መልእክተኞችን ላክሁ፦
በዮርዳኖስ ማዶ በኢያሪኮ በኩል ከሮቤል ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ በሚሶን ምድረ በዳ ቦሶርንና መሰማርያዋን፥ ኢያዜርንና መሰማርያዋን፤
ከጋድም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገለዓድ ውስጥ ራሞትንና መሰማርያዋን፥ ቃሚንንና መሰማርያዋን፤