La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 19:50 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በኤ​ፍ​ሬም ተራ​ራማ ሀገር ያለ​ች​ውን ተም​ና​ሴራ የም​ት​ባ​ለ​ውን የፈ​ለ​ጋ​ትን ከተማ ሰጡት፤ ከተ​ማም ሠርቶ ተቀ​መ​ጠ​ባት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር ባዘዘውም መሠረት በኰረብታማው የኤፍሬም ምድር የምትገኘውን ተምናሴራ የምትባለውን የፈለጋትን ከተማ ሰጡት፤ እርሱም ከተማዪቱን ሠራ፤ መኖሪያውም አደረጋት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በኤፍሬም ተራራማ አገር ያለችውን እንዲሰጡት የጠየቃቸውን ተምናሴራ የምትባለውን ከተማ እንደ ጌታ ትእዛዝ ሰጡት፤ ከተማም ሠርቶ ተቀመጠባት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔርም ባዘዘው መሠረት በኮረብታማው በኤፍሬም አገር እንዲሰጡት የጠየቃቸውን ቲምናትሴራሕ ተብላ የምትጠራውን ከተማ ሰጡት፤ ያቺንም ከተማ እንደገና ሠርቶ መኖሪያው አደረጋት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በኤፍሬም ተራራማ አገር ያለችውን ተምናሴራ የምትባለውን የፈለጋትን ከተማ እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ ሰጡት፥ ከተማም ሠርቶ ተቀመጠባት።

Ver Capítulo



ኢያሱ 19:50
6 Referencias Cruzadas  

ስማ​ቸ​ውም ይህ ነበረ፤ በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር በኤ​ፍ​ሬም የሖር ልጅ ቢዖር፥


የሴት ልጁም ስም ሲአራ ነበረ፤ በዚ​ያም በቀ​ሩት ታች​ኛ​ው​ንና ላይ​ኛ​ውን ቤት​ሖ​ሮ​ንን ሠራ የኡ​ዛ​ንም ልጁ ሠይራ ነበረ፤


ከኤ​ፍ​ሬም ነገድ የነዌ ልጅ አውሴ፤


ምድ​ሩ​ንም ሁሉ በየ​ድ​ን​በሩ ርስት እን​ዲ​ሆን ከፍ​ለው ከጨ​ረሱ በኋላ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለነዌ ልጅ ለኢ​ያሱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ርስት ሰጡት።


በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ሬም ሀገር በገ​ዓስ ተራራ በሰ​ሜን ባለ​ችው በር​ስቱ ዳርቻ በተ​ም​ና​ሴራ ቀበ​ሩት። በዚ​ያም ከግ​ብፅ በወጡ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በገ​ል​ገላ የገ​ረ​ዘ​ባ​ቸ​ውን የድ​ን​ጋይ ባል​ጩ​ቶ​ችን እር​ሱን በቀ​በ​ሩ​በት መቃ​ብር ከእ​ርሱ ጋር ቀበሩ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ አሉ።


በተ​ራ​ራ​ማዉ በኤ​ፍ​ሬም ሀገር በገ​ዓስ ተራራ በሰ​ሜን ባለ​ችው በር​ስቱ ዳርቻ በተ​ም​ና​ሴራ ቀበ​ሩት።