ኢያሱ 19:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አርኮብ፥ አፌቅ፥ ረአውም ደግሞ ነበሩ፤ ሃያ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም የዑማን፣ የአፌቅንና የረአብን ምድር ይጨምራል። በዚህም ሃያ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው ይገኛሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዑማ፥ አፌቅ፥ ረዓብ ደግሞ ነበሩ፤ ሀያ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዑማ፥ አፌቅና ረሖብ ተብለው የሚጠሩትን ኻያ ሁለት ከተሞችና በዙሪያቸው የሚገኙ ታናናሽ ከተሞችን ይጨምራል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዑማ፥ አፌቅ፥ ረአብ ደግሞ ነበሩ፥ ሀያ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው። |
ድንበሩም ወደ ራማ፥ ወደ መስፋጥ ምንጭ ወደ ጢሮስ ይዞራል፤ ድንበሩም ወደ ኢያሴፍ ይዞራል፤ መውጫውም በሌብና በኮዛብ በኩል ወደ ባሕሩ ነበረ፤
አሴርም የዓኮ ነዋሪዎችን አላጠፋቸውም፤ ነገር ግን ገባሮች ሆኑላቸው፤ የዶር ነዋሪዎችንና የሲዶን ነዋሪዎችን፥ የደላፍንም ነዋሪዎች፥ የአክሶዚብንና የሄልባን፥ የአፌቅንና የረዓብንም ሰዎች አላጠፉአቸውም።
ፍልስጥኤማውያንም ጭፍሮቻቸውን ሁሉ ወደ አፌቅ ሰበሰቡ፤ እስራኤላውያንም በኢይዝራኤል ባለው ውኃ ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ።
በእነዚያም ወራት እንዲህ ሆነ። ፍልስጥኤማውያን ለጦርነት በእስራኤላውያን ላይ ተሰበሰቡ። እስራኤልም ሊዋጉአቸው ወጡ፤ በአቤኔዜር አጠገብም ሰፈሩ፤ ፍልስጥኤማውያንም በአፌቅ ሰፈሩ።