La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 18:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሰዎ​ችም ተነ​ሥ​ተው ሄዱ፤ ኢያ​ሱም ምድ​ሩን ሊጽፉ የሄ​ዱ​ትን፥ “ሂዱ፤ ምድ​ሩ​ንም ዞራ​ችሁ ጻፉት፤ ወደ እኔም ተመ​ለሱ፤ በዚ​ህም በሴሎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዕጣ አጣ​ጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሰዎቹ የምድሪቱን ሁኔታ ለማጥናትና ለመመዝገብ ጕዞ ሲጀምሩ ኢያሱ፣ “ሄዳችሁ የምድሪቱን ሁኔታ አጥኑና በዝርዝር ከጻፋችሁ በኋላ ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም እዚሁ ሴሎ በእግዚአብሔር ፊት ዕጣ እጥልላችኋለሁ” አላቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሰዎቹም ተነሥተው ሄዱ፤ ኢያሱም ምድሩን ተመልክተው ሊጽፉ የሄዱትን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ “ሂዱ፥ ምድሩንም ዞራችሁ እዩና ጻፉት፥ ወደ እኔም ተመለሱ፤ በዚህም በሴሎ በጌታ ፊት ዕጣ እጥልላችኋለሁ።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሰዎቹም የምድሪቱን ሁኔታ ለማጥናት ከመሄዳቸው በፊት ኢያሱ፥ “ወደ ምድሪቱ ሁሉ ሂዱ፤ አቀማመጥዋንም አጥንታችሁ መዝግቡ፤ ወደ እኔም ተመልሳችሁ ኑ፤ እኔም በዚህ በሴሎ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ዕጣ እጥልላችኋለሁ” የሚል መመሪያ ሰጣቸው፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሰዎችም ተነሥተው ሄዱ፥ ኢያሱም ምድሩን ሊጽፉ የሄዱትን፦ ሂዱ፥ ምድሩንም ዞራችሁ ጻፉት፥ ወደ እኔም ተመለሱ፥ በዚህም በሴሎ በእግዚአብሔር ፊት ዕጣ አጣጥላችኋለሁ ብሎ አዘዛቸው።

Ver Capítulo



ኢያሱ 18:8
13 Referencias Cruzadas  

ተነሣ፤ በም​ድር በር​ዝ​መ​ቷም፥ በስ​ፋ​ቷም ዙር፤ እር​ስ​ዋን ለአ​ን​ተና ለዘ​ርህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እሰ​ጣ​ለ​ሁና።”


እር​ሱም ዕጣ ጣለ​ባ​ቸው፤ እጁም ከፈ​ለ​ች​ላ​ቸው፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይሰ​ማ​ሩ​ባ​ታል፤ ከት​ው​ል​ድም እስከ ትው​ልድ ድረስ ይወ​ር​ሱ​አ​ታል፤ በው​ስ​ጥ​ዋም ያር​ፉ​ባ​ታል።


አሁ​ንም ወን​ድ​ማ​ችን ይታ​ነጽ ዘንድ ሰላ​ምን እን​ከ​ተ​ላት።


አሁ​ንም ይህን ምድር ለዘ​ጠኙ ነገድ፥ ለም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ርስት አድ​ር​ገህ ክፈ​ለው። ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ጀምሮ በም​ዕ​ራብ እስ​ካ​ለው ታላቁ ባሕር ድረስ ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ታላቁ ባሕር ይሆ​ናል።”


የይ​ሁ​ዳም ነገድ ድን​በር በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ከኤ​ዶ​ም​ያስ ዳርቻ፥ ከጺን ምድረ በዳ ጀምሮ በዐ​ዜብ በኩል እስከ ቃዴስ ድረስ ነው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በሴሎ ተሰ​በ​ሰቡ፤ በዚ​ያም የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ተከሉ፤ ምድ​ሩም ጸጥ ብሎ ተገ​ዛ​ላ​ቸው።


ኢያ​ሱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሴሎ ዕጣ አጣ​ጣ​ላ​ቸው።


እና​ን​ተም ምድ​ሪ​ቱን በሰ​ባት ክፍል ክፈ​ሏት፤ ወደ እኔም ወዲህ አም​ጡ​ልኝ፤ በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በዚህ ዕጣ አጣ​ጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


ሰዎ​ቹም ሄደው ምድ​ሩን ዞሩ፥ አዩ​ትም፤ እንደ ከተ​ሞ​ችም በሰ​ባት ክፍል ከፈ​ሉት፤ በመ​ጽ​ሐ​ፍም ጻፉት፤ ወደ ኢያ​ሱም አመጡ።


ሳኦ​ልም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ ለእኔ ለባ​ሪ​ያህ ዛሬ ያል​መ​ለ​ስ​ህ​ልኝ ስለ ምን​ድን ነው? ይህች በደል በእኔ፥ በልጄ በዮ​ና​ታ​ንም እንደ ሆነች አቤቱ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ ተና​ገር። ዕጣው ይህን የሚ​ገ​ልጥ ከሆነ ለሕ​ዝ​ብህ ለእ​ስ​ራ​ኤል እው​ነ​ትን ግለጥ፥” አለ። ዕጣም በዮ​ና​ታ​ንና በሳ​ኦል ላይ ወጣ፤ ሕዝ​ቡም ነፃ ወጣ።