ኢያሱ 17:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዕጣቸውም በዮርዳኖስ ማዶ ከአለው ከገለዓድና ከባሳን ሀገር በቀር ለምናሴ ዐሥር ዕጣ ሆነ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምናሴም ከገለዓድና ከባሳን ምድር ሌላ፣ ዐሥር ቦታ የሚደለደል የመሬት ክፍል በዮርዳኖስ ምሥራቅ ነበረው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዮርዳኖስ ማዶ ካለው ከገለዓድና ከባሳን አገር ሌላ ለምናሴ ዐሥር ዕጣ ደረሰው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምናሴ በዮርዳኖስ ወንዝ በስተምሥራቅ ከሚገኙት ከገለዓድና ከባሳን ጋር በተጨማሪ ዐሥር ዕጣ እንዲደርሰው ተደርጎአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዮርዳኖስ ማዶ ካለው ከገለዓድና ከባሳን አገር ሌላ ለምናሴ አሥር ዕጣ ሆነ፥ |
ገለዓድንም፥ የጌሴሪያውያንንና የመከጢያውያንን ዳርቻ ሁሉ፥ የአርሞንዔምንም ተራራ ሁሉ፥ ባሳንንም ሁሉ፥ እስከ ሰልካ ድረስ፥
የዮሴፍም ልጆች ኢያሱን፥ “እኛ ብዙ ሕዝብ ስንሆን እስከ አሁንም እግዚአብሔር ስለ ባረከን ለምን አንድ ክፍል፥ አንድም ዕጣ ብቻ ርስት አድርገህ ሰጠኸን?” ብለው ወቀሱት።
እነርሱም ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛርና ወደ ነዌ ልጅ ወደ ኢያሱ ወደ አለቆችም ቀርበው፥ “እግዚአብሔር በወንድሞቻችን መካከል ርስት እንዲሰጠን በሙሴ እጅ አዘዘ” አሉ፤ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ከአባታቸው ወንድሞች ጋር ርስት ሰጣቸው።
የምናሴ ሴቶች ልጆች በወንድሞቻቸው መካከል ርስት ተቀብለዋልና፤ የገለዓድም ምድር ለቀሩት ለምናሴ ልጆች ሆኖአልና።
ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ሙሴ በባሳን ውስጥ ርስት ሰጥቶአቸው ነበር፤ ለቀረው ለእኩሌታው ግን ኢያሱ በዮርዳኖስ ማዶ በባሕር በኩል በወንድሞቻቸው መካከል ርስት ሰጣቸው። ኢያሱም ወደ ቤታቸው በአሰናበታቸው ጊዜ እንዲህ ብሎ መረቃቸው፦