እርሱም በጨው ሸለቆ ከኤዶምያስ ዐሥር ሺህ ሰው ገደለ፤ ሴላንም በጦርነት ወስዶ ስምዋን እስከ ዛሬ ድረስ “ዮቅትኤል” ብሎ ጠራት።
ኢያሱ 15:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አዶላል፥ መሴፋ፥ ይቃሩል፥ ለኪስ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዲልዓን፣ ምጽጳ፣ ዮቅትኤል፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዲልዓን፥ ምጽጳ፥ ዮቅትኤል፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዲልዓን፥ ምጽጳ፥ ዮቅጥኤል፥ |
እርሱም በጨው ሸለቆ ከኤዶምያስ ዐሥር ሺህ ሰው ገደለ፤ ሴላንም በጦርነት ወስዶ ስምዋን እስከ ዛሬ ድረስ “ዮቅትኤል” ብሎ ጠራት።
በምሥራቃዊ ባሕር ዳርቻ ወዳለው ወደ ከነዓናዊው፥ ወደ አሞሬዎናዊውም፥ ወደ ኬጤዎናዊውም፥ ወደ ፌርዜዎናዊውም፥ በተራራማውም ሀገር ወዳለው ወደ ኢያቡሴዎናዊው፥ በቆላማውና በመሴፋ ወዳለው ወደ ኤዌዎናዊዉም ላከ።
የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ወጡ፤ ማኅበሩም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ፥ ከገለዓድም ሰዎች ጋር፥ ወደ እግዚአብሔር ወደ መሴፋ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰበሰቡ።
የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ወደ መሴፋ ስላልወጣ ሰው፥ “እርሱ ፈጽሞ ይገደል” ብለው ታላቅ መሐላ ምለው ነበርና፥ “ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ወደ ጉባኤ ወደ እግዚአብሔር ያልወጣ ማን ነው?” አሉ።
በየዓመቱም ወደ ቤቴል፥ ወደ ጌልጌላና ወደ መሴፋ ይዞር ነበር፤ በእነዚያም በተቀደሱ ስፍራዎች ሁሉ በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር።